Health Services
የሲያትል ትምህርት ቤት ነርሶች በርቀት ትምህርት ወቅት ተማሪዎችን እና ቤተሰቦችን ለማገዝ እና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ወደ ትምህርት ቤት ለመመለስ እየሰሩ ናቸው።
የአዲሱየትምህርትዓመትአስፈላጊየጤናመረጃ
ክትባቶችንወስደዋል?
ልጅዎ ለትምህርት ቤት ስለሚያስፈልገው ክትባት በተመለከተ ከጤና አገልግሎቶች ደብዳቤ ከተቀበሉ እባክዎን ልጅዎ በደብዳቤው ውስጥ የተዘረዘሩትን ክትባት (ቶች) ማግኘቱን ያረጋግጡ ፡፡ የክትባት ማስረጃውን ለት/ቤቱ ነርስ ይላኩ ወይም የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ(ሃኪምዎ) ማስረጃዉን ለነርሷ ፋክስ እንዲያደርግ ያድርጉ ።የክትባት መስፈርቶች በዚህ አገናኝ ላይ ይገኛሉ (Immunization requirements)
የኮቪድ -19 መስፋፋትን እንዴት እንደሚገድቡ ይወቁ እና እነዚህን እርምጃዎች ይለማመዱ:
- ከሌሎች ሰዎች ኣካላዊ ንክኪ ያስወግዱ
- ከሌሎች ሰዎች ጋር በሚሆኑበት ጊዜ አፍንጫዎን እና አፍዎን በጭምብል ይሸፍኑ
- እጆችዎን አዘውትሮው ይታጠቡ
- እጆችዎን ከፊትዎ ያርቁ
- ከሌሎች ሰዎች በ 6 ጫማ ርቀት ይቆዩ
- ሲያስነጥሱ እና ሲስሉ ይሸፈኑ
- ልጅዎ ምልክቶች ሊኖሩት ይችላል ብለው ካሰቡ የ Public Health SCAN program ይጠቀሙ
- Free COVID testing
የጤናዝመናዎች
እባክዎን በልጅዎ ደህንነት እና ትምህርት ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር የሚችል ማንኛውንም የጤና ችግር ለትምህርት ቤቱ ነርስ ሪፖርት ያድርጉ ፡፡
ዓመታዊ የተማሪ ጤና ማዘመኛ(Annual Student Health Update) ቅጽ ይሙሉ ወይም :
- the Source ን በመስመር ላይ ይጎብኙ ወይም
- በመጀመርያ የትምህርት ዓመት ከትምህርት ቤት በሚላከው ፓኬት ውስጥ የተካተተውን የወረቀት ቅጅ ይሙሉ
እንዲሁም ነርሷን በቀጥታ በስልክ ወይም በኢሜል ማነጋገር ይችላሉ ፡፡
ተማሪዎንወደየትምህርትቤትየጤናማእከልያስመዝግቡ!
ልጅዎ በዲስትሪክቱ ውስጥ ወደ ማናቸውም የት / ቤት የጤና ማዕከል መሄድ ይችላል።ነፃ ነው!
ለእርስዎ ቅርብ የሆነውን የትምህርት ቤት የጤና ማእከል ለመፈለግ ይህንን አገናኝ Locate a School Based Health Center near you ወይም interactive map ጠቅ ያድርጉ።
የመድኃኒትቅጽ
ወደት/ቤታችንለመመለስአሁኑኑይዘጋጁ /በትምህርትቤትለሚወሰዱመድኃኒቶችፈቃድ (Authorization for Medications Taken at School)እንዲሞሉየጤናአገልግሎትአቅራቢዎን(ሃኪምዎን)ይጠይቁ።
- እያንዳንዱ መድሃኒት የራሱ የሆነ ቅጽ ይፈልጋል
- የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ(ሃኪምዎ)መፈረም አለበት
- እርስዎ ቅጹን መፈረም አለብዎት
ይህ ለሁሉም መድኃኒቶች ይፈለጋል፡፡
መድሃኒት
ወደትምህርትቤታችንስንመለስሁሉምመድሃኒቶችበመድሃኒትቤትበታተመውየመጀመርያመያዣቸው (የመጀመርያዕቃዎቻቸው) መሆንአለባቸው። የድንገተኛጊዜመድሃኒቶችበትምህርትቤቱየመጀመሪያቀንወይምከዚያበፊትበትምህርትቤቱህንፃውስጥመኖርአለባቸው።
* የመድኃኒቱ የማብቂያ ቀናት ያረጋግጡ! የትምህርት ዓመቱን ሙሉ የሚቆዩ መድኃኒቶችን ለማግኘት ይሞክሩ።
በዚሁጽሁፍየተገናኙፀጋዎች :
በርቀት ትምህርት ወቅት ክፍት የሚሆኑ በትምህርት ቤት የተመሰረቱ የኪንግ ካውንቲ የጤና ማዕከሎች ዝርዝር