Seattle Public Schools

Who to Contact (am)

ስጋቶችን የመፍታት እርምጃዎች

ደረጃ 1: መምህሩን ወይም አማካሪውን ማነጋገር

አብዛኛዎቹ ስጋቶች በተማሪዎ አስተማሪ ወይም በትምህርት ቤት ሰራተኞች እርዳታ ሊፈቱ ይችላሉ።

  • ለከቅድመ መደበኛ ትምህርት እስከ 5ኛ ክፍል፣የተማሪዎን መምህር ያነጋግሩ።
  • ለከ6ኛ-12ኛ ክፍል፣የተማሪዎን መምህር ወይም አማካሪ ያነጋግሩ።

የትምህርት ቤት ሰራተኞች ልጅዎን ለመርዳት እዚህ አሉ።አስተማሪዎች ስጋቶችን በተቻለ ፍጥነት እንዲያውቁት ከተደረገ ችግሮችን ለመፍታት ሊረዱ ይችላሉ።አስተማሪዎች ብዙ ተማሪዎችን እንደሚረዱ እባክዎን ልብ ይበሉ።ስለትእግስትዎ እናመሰግናለን።

ደረጃ 2: የትምህርት ቤቱን ርዕሰ መምህር ማነጋገር

Iስጋትዎ አልተፈታም ብለው ካመኑ የትምህርት ቤቱን ርእሰ መምህር ያነጋግሩ።

ደረጃ 3: የዲስትሪክት ጽሕፈት ቤት ማነጋገር

Iከትምህርት ቤትዎ ርእሰመምህር ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ስጋትዎ ካልተፈታ፣በሁኔታዎ ላይ በመመስረት ከታች ካሉት አማራጮች አንዱን ያነጋግሩ።


የደህንነት ስጋቶችን ሪፖርት ማድረግ

በአደጋ ጊዜ፣ወደ 911 ይደውሉ

ስለሚከተሉት የጥንቃቄ እና የደህንነት ዲፓርተመንት ያነጋግሩ

  • የተማሪዎች ወይም የሰራተኞች ደህንነት ስጋቶች እና ጥያቄዎች
  • የአደጋ ጊዜ ዝግጁነት መረጃ

የጥንቃቄ እና የደህንነት ዲፓርትመንት በቀን ለ24 ሰዓታት፣በዓመት ለ365 ቀናት ይሰራል።ለአስቸኳይ ጉዳዮች፣የጥንቃቄ እና የደህንነት ዲፓርትመንት በስልክ ቁጥር 206-252-0707 ያነጋግሩ።


የተማሪ ጉልበተኝነት ወይም አድልዎ

ስለሚከተሉት ስጋቶች የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች የተማሪ ሲቪል መብቶች ፅ/ቤት ያነጋግሩ

  • ጉልበተኝነት
  • አድልዎ
  • ትንኮሳ
  • ማስፈራራት
  • ወሲባዊ ጥቃት

ሪፖርቶች በቃልም ሆነ በጽሁፍ ሊቀርቡ ይችላሉ።


የዲስትሪክቱን እንባ ጠባቂ ያነጋግሩ

ማንን ማነጋገር እንዳለቦት እርግጠኛ ካልሆኑ ወይም ትምህርት ቤቱ ወይም ዲፓርትመንቶቹ ፖሊሲን ወይም ፍትሃዊ አሰራርን እንደማይከተሉ ከተሰማዎት፣እባክዎ የዲስትሪክቱን እንባ ጠባቂ ፅ/ቤት ያነጋግሩ። እንባ ጠባቂው በትምህርት ቤት ደረጃ ሊፈቱ የማይችሉ ችግሮችን ለመፍታት ከቤተሰቦች እና ከትምህርት ቤቶች ጋር ይሰራል።