Seattle Public Schools

Resources

Transportation

መጓጓዣ

ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች በመመደብያ ትምህርት ቤታቸው(attendance area) የሚኖሩ ነገር ግን  ከትምህርት ቤቱ የእግር መንገድ( school’s walk zone) ውጪ ላሉ ተማሪዎች ነጻ መጓጓዣ ይሰጣል።

አንድ ተማሪ እንደ መስማት የተሳናቸው እና የመስማት ችግር ያለባቸው አገልግሎቶች በመሳሰሉት ፕሮግራሞች ከተመደበ እና እነዚህ ፕሮግራሞች በየመመደብያ ትምህርት ቤት(neighborhood (attendance) ) የማይገኙ ከሆነ፣አብዛኛውን ጊዜ የመጓጓዣ አገልግሎት ይሰጣል።

የመጓጓዣ ብቁነት መመሪያዎች

  • የ 1ማይል የእግር ጉዞ ወሰን ያላቸው የአንደኛ ደረጃ እና የK-8 ትምህርት ቤቶች።ብቁ የሆኑ ተማሪዎች በዋናነት የትምህርት ቤት የቢጫ አውቶቡሶች አገልግሎት ያገኛሉ።
  • የ 2 ማይል የእግር ጉዞ ወሰን ያላቸው የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች።የትምህርት ቤት የቢጫ አውቶቡሶች ወይም የሜትሮ ORCA ካርድ አገልግሎት ያገኛሉ።
  • የ2 ማይል የእግር ጉዞ ወሰን ያላቸው የ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች።የORCA ካርድ አገልግሎት ያገኛሉ።

ልጅዎ ለመጓጓዣ ብቁ መሆኑን ለማየት የመመደብያ ወይም የአማራጭ ትምህርት ቤቶች የመጓጓዣ ካርታ ይጠቀሙ።

በእግር እና በብስክሌት ወደ ትምህርት ቤት መሄድ!

ወደ ትምህርት ቤት በእግር እና ብስክሌት መሄድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ፣በትምህርት ቤቶች አካባቢ ያለውን መጨናነቅ እና ብክለት ለመቀነስ እንዲሁም ማህበረሰብ ለመፍጠር አስደሳች መንገድ ነው።ወደ ትምህርት ቤት በእግር እና በብስክሌት የሚጓዙ ተማሪዎች የበለጠ ንቁ እና ለመማር ዝግጁ እንደሚሆኑ ጥናቶች ያሳያሉ! በእግር እና በብስክሌት ወደ ትምህርት ቤት መሄድ!

የትምህርትቤትአስተማማኝመንገዶች

ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ ብስክሌት መንዳት እና መራመድ ጥሩ መንገዶች ናቸው። ወደ ትምህርት ቤትዎ የሚወስድ ደህንነቱ የተጠበቀ የእግር እና የብስክሌት መንገዶችን ለማግኘት የሲያትል ከተማ መስተጋብራዊ ካርታን ይጠቀሙ።

የአውቶቡስመዘግየት

የአውቶቡስ መስመሮች አንዳንድ ጊዜ በትራፊክ፣በአየር ሁኔታ፣በግንባታ ወይም በሌሎች ሁኔታዎች ይዘገያሉ።

አውቶቡስዎ ዘግይቶ ከሆነ፣ተማሪዎ በአውቶቡስ ማቆሚያ ላይ እንዲቆይ እንመክራለን።አውቶቡስ ቢዘገይ ምን ማድረግ እንዳለብዎት እባክዎ ከተማሪዎ ጋር እቅድ ያውጡ እንዲሁም ይወያዩ።

ቢያንስ 15 ደቂቃ ዘግይተው ይመጣሉ ተብሎው ሪፖርት የተደረጉትን የአውቶቡስ መስመሮች ይመልከቱ።