Seattle Public Schools

ስለ 2022-23 የታቀዱ የደውል ጊዜያት ተጨማሪ መረጃ ያግኙ

Summary: Seattle Public Schools ከመስከረም 2022 ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የትምህርት መጀመሪያ ሠዓት ለውጥ ለማድረግ አቅዷል።

የግንቦት 3 ፕሮግራም: ስለ 2022-23 የታቀዱ የደውል ጊዜያት ተጨማሪ መረጃ ያግኙ

እባክዎ ማክሠኞ ግንቦት 3 የ2022-23ን በመላው ዲስትሪክቱ ያለውን የደወል ሠዓት ለውጥ እቅድ ለመግለጽ የተያዘውን የኦንላይን ፕሮግራም ይቀላቀሉ።

Seattle Public Schools ከመስከረም 2022 ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የትምህርት መጀመሪያ ሠዓት ለውጥ ለማድረግ አቅዷል።

የደወል ሠዓታት ላይ ለውጥ ለማድረግ ለሁሉም ቤተሠቦች እና ሠራተኞች ተገቢውን ማስተካከያ እንዲያደርጉ የሚያስገድዳቸው መሆኑን እናውቃለን። ይህን ለውጥ ማድረግ የሚመከረው ተማሪዎች ሁልጊዜም በትምህርት ሠዓት ትምህርት ቤት የሚደርሱ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው።

በዚህ ፕሮግራም ላይ ከዲስትሪክቱ አመራሮች ስለ SPSየደውል ሰዓታት እቅድ የሚቀርቡ ዝርዝር መረጃዎችን እና በተደጋጋሚ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች የሚሠጡ መልሶችን ይሠማሉ።

የAmerican Sign Language (ASL), Amharic, Cantonese, Somali, Spanish, እና Vietnamese አስተርጓሚዎች ይገኛሉ። ከፕሮግራሙ በኋላ ቀረጻው በደውል ሠዓት ለውጦች ድረገጽ ላይ ይለቀቃል።   

ቀን: ማክሠኞ, ግንቦት 3/2022 (May 3, 2022)
ሠዓት: 5:30 p.m.

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ እባክዎ የኛን የታቀደ የደውል ሠዓት ለውጦች ድረገጽ 2022-23ን ይጎብኙ። 

You may also be interested in

A graphic with clock and bell

በታቀዱት የደወል ጊዜ ለውጦች ዝመናዎች

እነዚያን ተግዳሮቶች ለመፍታት ብዙ ጊዜ እየወሰድን ነው።…

የትምህርት የመጀመሪያ ሰዓት ለውጥ ፕሮፖዛል 2022-23

ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (SPS) የቀጣዩ የትምህርት ዓመት የደወል ጊዜ (የትምህርት መጀመሪያ እና መጨረሻ ጊዜ) እንዲቀየር ሐሳብ አቅርቧል።…
A graphic with clock and bell

በ2022-23 የትምህርት ዓመት የትምህርት መጀመርያ ሰዓት የደረገ ለውጥ የለም

ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ሰዓት ለመቀየር የቀረበው ሃሳብ አስመልክቶ ከብዙ ቤተሰቦች ስጋቶችን ሰምተናል።…