Seattle Public Schools

State of the District

Seattle Public Schools State of the District 2022 

የትምህርት ቦርድ ፕሬዝዳንት Hersey 

ዛሬ ምሽት ስለተቀላቀሉን እናመሰግናለን።እንኳን ወደ የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች የ2020 መግለጫ በደህና መጡ። 

ከመጀመራችን በፊት፣ሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች በየPuget Sound Coast Salish ህዝቦች ቅድመ አያቶች መሬቶች እና ባህላዊ ግዛቶች ላይ መሆናችንን እውቅና እንሰጣለን።በተለይ ለሀገራችን መመስረት፣ሀብትና እድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ጥቁር እና ቡናማ ህዝቦች ነፍስ እና ህይወት እውቅና መስጠት አስፈላጊ ነው። 

እነዚህ ምስጋናዎች ጅምር እንጂ ከተወዳጅ ማህበረሰባችን የተለያዩ ድምፆች ጋር የሚደረግ ትክክለኛ ግንኙነት እና ተሳትፎ መተኪያ አይደሉም።ያለማቋረጥ ሁኔታውን ስለታገላቹ እና እያንዳንዳችን የተሻለ እንድንሆን ስላረዳችሁን እናመሰግናለን።  

ሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች በስራ ቦታዎቻችን ላይ በተለይም ከትምህርታዊ ፍትህ በራቁ ተማሪዎች፣ስርአታዊ ዘረኝነትን እና መድሎዎችን ለማጥፋት ቁርጠኛ ነው።ለውጥ ለመፍጠር ከእኛ ጋር እንድትሰሩ እጋብዛለሁ። 

በዚህ ጊዜ፣የሲያትል ከተማ ከንቲባ ሳስተዋውቅ በታላቅ ክብር ነው።ከአሁኑ ከንቲባ – የሲያትልን ታሪክ የሚያንፀባርቅ እና የሲያትልን የወደፊት ተስፋ የሚያይ የሲያትል ልጅ – ለትምህርት ቤቶቻችን እና ለማህበረሰባችን የተሻለ ጓደኛ እና ሻምፒዮን ልንጠይቅ አልቻልንም።እባኮትን የሲያትል 57ኛ ከንቲባ – የተከበሩ Bruce Harrellን እንኳን ደህና መጡ በሉልኝ።  

ከንቲባ Harrell 

Dr. Brent Jones ድርጅታዊ ባህልን በመቀየር እና የPreK-12 ትምህርት ስርዓቶችን እና ድጋፎችን በመንደፍ ሁሉም ተማሪዎች እንዲበለፅጉ ለማድረግ ቁርጠኛ ነው።በስትራቴጂክ እቅድ፣በማህበረሰብ ተሳትፎ፣በለውጥ አስተዳደር እና በሰው ሃይል ሰፊ የመንግስት ሴክተር እውቀት ያለው ዶክተር ጆንስ የትምህርት ፍትህን ለማራመድ ምቹ ሁኔታዎችን እና ስርዓቶችን በመፍጠር ልምድ አሳይቷል። 

እንደ የቀድሞ የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች የፍትሃዊነት፣የሽርክና እና የተሳትፎ ኦፊሰር፣የዲስትሪክቱን የዕድል ክፍተቶችን በማስወገድ የተማሪዎች እና የቤተሰቦች የዘር ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅቷል።እሱ             በMLK King County፣በSeattle Public Schools፣በKent School District፣በSeattle Colleges፣እና በGreen River College በስራ አስፈፃሚነት አገልግሏል። 

እንደ ዋና ሃላፊ፣የዶ/ር ጆንስ ራዕይ የእያንዳንዱን ተማሪ ተሞክሮ ማረጋገጥ ነው: 

  • ከፍተኛ ጥራት ያለው የማስተማሪያ ጊዜ እና ሥርዓተ-ትምህርት፤ 
  • የራሳቸውን ማንነት ለማዳበር ሰፊ እድሎች፤ 
  • በጣም ምቹ እና ተቀባይ ሁኔታዎች፤ 
  • ከደረጃ በላይ እና የኮሌጅ ዝግጅት እና ጠንካራ ኮርሶች ማጠናቀቅ። 

ዶ/ር ጆንስ ጥልቅ የሆነ የማህበረሰብ ሥር ያለው እና የሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች እና የዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ኩሩ ምርት ነው።እሱ በትምህርት አስተዳደር የማስተርስ እና የ Ph.D. ዲግሪዎች ከኦስተን ቴክሳስ ዩኒቨርሲቲ አግኝቷል።ከቤተሰብ ጋር ጊዜ ማሳለፍ፣መሥራት፣የፈጠራ ፕሮጀክቶችን መሥራት እና የዘፈቀደ የደግነት ተግባራትን ማከናወን ያስደስተዋል። 

ዋና ሃላፊ Jones  

ከንቲባ ሃረል ለእንደዚህ አይነት ለጋስ መግቢያ እና እንዲሁም ለጠንካራ ድጋፍዎ እና አጋርነትዎ እናመሰግናለን። 

ስለቀጣይ አመራር እና የተማሪዎች ድጋፍ፣ለመላው የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች የዳይሬክተሮች ቦርድ ማመስገን እፈልጋለሁ። 

ከመጀመራችን በፊት እባኮትን ባለቤቴ፣Janine፣ስላደረገችው ድጋፍ እና ዛሬ ማታ እዚህ በመገኘትዋ እንዳመሰግን ፍቀድልኝ። 

ብዙ ልዩ እንግዶችም ተቀላቅለዋል:  

  • ከንቲባ Harrell 
  • የሲያትል የትምህርት እና የቅድመ መደበኛ ትምህርት ዲፓርትመንት Dr. Chappelle 
  • የሲያትል ፖሊስ ዲፓርትመንት ዋና ሃላፊ Diaz 
  • ሴናተር Saldana 
  • ከየJayapal እና የGovernor Inslee’s ፅ/ቤት የመጡ ተወካዎች  
  • ከ ሴናተር Patty Murray’s ፅ/ቤት የመጡ ተወካዎች  
  • የሲያትል የንግድ ምክር ቤት ዋና ሥራ አስፈፃሚ Rachel Smith፣የትምህርት ህብረት ዋና ዳይሬክተር፣Ms. Lisa Chick፣ 
  • እና ከ SCPTSA ውድ ጓዶቻችን፤ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል።  

እንዲሁም ውድ ተማሪዎቻችን፣ቤተሰቦች፣አስተማሪዎች፣የሕንፃ እና የአስተዳደር መሪዎች፣የሲቪክ ሹማምንቶች፣የንግድ ድርጅቶች፣የማህበረሰብ አቀፍ አጋሮች እና የሲያትል/ኪንግ ካውንቲ ነዋሪዎች ዛሬ ምሽት ወደዚህ የጋራ ቦታ መጋበዝ እፈልጋለሁ።ይህንን የትምህርት ዘመን እውን በማድረግ በእያንዳንዱ ደረጃ ከጎናችን ነበራችሁ። 

ዛሬ ማታ ለታታሪነትዎ፣ትብብርዎ እና አጋዥ ግብረ መልስዎ የተሰጠ ጊዜ ነው። 

የሲያትል ትምህርት ቤቶች ስኬት – ለእኔ ጥልቅ ግላዊ ነው። 

ዛሬ ማታ፣የሲያትል የህዝብ ት/ቤቶች አዲስ ዋና ሃላፊ ሁኜ በፊትዎ በመቆሜ ደስ ብሎኛል።በእኔ ላይ ስላላቹ እምነት አመሰግናሎህ።ክብር ይሰማኛል።እንዲሁም የተማሪዎቻችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ ይህንን ዲስትሪክት እና ህብረተሰባችን ለማገልገል ቃል እገባለሁ። 

ብዙዎቻችሁ እንደምታውቁት ሲያትል የህዝብ ቤቶች የእኔ ቅርስ ነው።እኔ ከሲያትል ነኝ፣እናቴ በሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ያስተማረችኝ ቦታ ነው።እኔ የዘር መለያየት ፖሊሲ በሚያበቃበት ጊዜ ወደ ትምህርት ቤት ገባሁ፣እና የፍራንክሊን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ኩሩ ምሁር ነኝ።Go Quakers! ታላቁ የህዝብ ትምህርት ቤታችን ለመምራት በ ግንቦት 2021 የቀረበውን ጥሪ ከመመለሴ በፊት የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች የሰው ሀብት መሪ እና የፍትሃዊነት እና የአጋርነት መሪ ሁኜ ሰርቻለሁ።ባለፈው ፀደይ፣ሴቷ ልጄ ከ Cleveland ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስትመረቅ በመመልከቴ ክብር ተሰምቶኛል።ይህ ጉዞ – እና የሲያትል ት / ቤቶች ስኬት – ለእኔ በጣም ጥልቅ ነው። 

ግልጽ ላድርግ፣ያለፉት በርካታ ወራት ለተማሪዎቻችን፣ለቤተሰቦቻችን እና ለአስተማሪዎቻችን ቀላል አልነበሩም። እንደ እርስዎ፣የበአካል ትምህርት ቶሎ ብሎ እንዲጀመር ተስፋ ነበረኝ።ትኩረታችን የጥረታችን አስኳል የሆነውን የ180 የልህቀት የትምህርት ቀናት ከትምህርታዊ ፍትህ የራቁ የቀለም ተማሪዎቻችን ጋር በመሆን እውን ማድረግ ነው።የሲያትል ልቀት ቃል ኪዳን ከDelta ወደ Omicron variant of COVID-19 

ስንሸጋገር በድጋሚ ተፈትኗል። 

ሆኖም፣ የትምህርት ቤቶቻችን መሪዎች፣አስተማሪዎች፣ተማሪዎች እና ቤተሰቦች ቀጣይነት ያለው የመቋቋም ችሎታ ይህ የትምህርት ዓመት በተሳካ እንዲሄድ እና በጣም ተስፋ ሰጪ እንዲሆን ኣድርጎታል።በመስከረም 1፣ተማሪዎች በተሻለ ሁኔታ ሊማሩበት ወደሚችሉበት ትምህርት ቤት ሲመለሱ በደስታ ተቀብለናል።የትምህርት እና የህዝብ ጤና ኤጀንሲ በጋራ በመስራት ትምህርት ቤቶችን ክፍት አድርገናል፤አስተማሪዎች የርቀት፣የቅይጥ እና የሁለቱም ትምህርት ያለማቋረጥ መስጠት ችለዋል።  

አንድ ላየ ሁነን፣የሚከተሉትን አሉን:  

  • ለኮቪድ መከላከል $50m+ ኢንቨስት ተደርጓል  
  • የክትባት ክሊኒኮቻችን ከ13,500 በላይ ተማሪዎችን አገልግሏል 
  • 79% የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ የተከተቡ መሆናቸውን ተረጋግጧል 
  • በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ ከ35ሺህ በላይ ሰዎች የኮቪድ-19 ምርመራ አድርጓል  

ከትምህርት አመቱ መጀመሪያ ጀምሮ፣ሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች እና ትምህርት ቤቶች እንዲስተካከሉ ድጋፍ አድርጓል።አስተማሪዎች እና የትምህርት ቤት መሪዎች ያለፉት ሁለት ዓመታት ከተማሪዎች ጋር በክፍል ውስጥ የሚገጥሟቸውን አዳዲስ ፈተናዎች እንዴት እንደሚያሸንፉ አዳዲስ ፈጠራዎችን መፍጠር ቀጥለዋል። 

ምንም እንኳን ከፍተኛ መሰናክሎች ቢኖሩም፣በሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ታላላቅ ነገሮች መከናወናቸውን እራሳችንን ማስታወስ አለብን።የሲያትል አካባቢ የወደፊት ጤንነት ለማየት በጣም ጓጉተናል እንዲሁም ገጹን ወደ ብሩህ ቀናት ለመቀየር ዝግጁ ነው። 

በጉጉት ወደምንጠብቀው የወደፊት ህይወታችን ስንገባ፣ሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች በመስቀለኛ መንገድ ላይ ይቀመጣል።ከወረርሽኝ መዘጋት፣የዘር ስሌት እና ቀጣይነት ያለው አለመረጋጋት ስንወጣ፣የሲያትል ትምህርት አዲስ የፈጠራ ተራማጅ እንዲሆን፣ትምህርትን እንደገና ለማሰብ እና ለውጥ ለማምጣት ይህንን ጉልበት እና የተማርነውን ትምህርት መጠቀም አለብን። 

በመጀመሪያ የሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ምን ላይ ጠንካራ እንደሆነ ልንገራችሁ።በሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች፣የማስተማር እና የመማር ሂደት  በደንብ እናካሂዳለን። 

  • የ9ኛ ክፍል ተማሪዎቻችን ለመመረቅ በዝግጅት ላይ ናቸው፣በ3ዓመታት ውስጥ በጊዜ ያጠናቀቁ የተማሪዎች መጠን ከ 85% ወደ 92% አድጓል። 
  • በ2020 እና 2021 መካከል የSeattle’s Promise programን የሚጠቀሙ የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ተመራቂዎች የ19% ጭማሪ አይተናል። 
  • ሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች አሁን 100 የሚሆኑ የአካል ጉዳተኛ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ተማሪዎችን ጨምሮ በ66 ክፍሎች 1300 የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ይቀበላል። 
  • የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የSTEM፣የIB እና የAP ኮርሶችን ጨምሮ የላቁ ኮርሶችን በመውሰድ ከስቴቱ አማካኝ ወይም ከዚያ በላይ ናቸው። 
  • የአፍሪካውያን አሜሪካውያን ተማሪዎችን እና ከትምህርት ፍትህ የራቁ የቀለም ተማሪዎችን ጨምሮ የተማሪዎች የምረቃ መጠን እየተሻሻለ ነው።  

በራኒየር ቪው አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመማር ደስታ ምን እንደሚመስል ላሳያችሁ። 

እኛ ስልጣን የሌላቸው እና በፍትህ የከፋ ግፍ ለደረሰባቸው ሰዎች ለማገዝ ጠንክረን ለመቆም በግልፅ ወስነናል። ለጥቁር ወንድ ልጆቻችን እና ታዳጊዎቻችን የሚሰራ ስርዓት የመገንባት ስልታዊ እቅድ አለን።ፍትህ የሚሰጡ እና ማህበረሰብን የሚያበረታቱ ስርዓቶች፣አወቃቀሮች እና ባህሪያት እንድናዳብር የሚያስገድዱ ግቦች እና ጥበቃዎች አዘጋጅተናል።ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ከትምህርታዊ ፍትህ የራቁ የቀለም ተማሪዎች፣እንዲሁም እያንዳንዱ ተማሪ ለኮሌጅ፣ለሥራ እና ለህይወት ዝግጁ እስኪሆኑ ድረስ ለማዘጋጀት ቃል ገብተዋል። 

የስትራቴጂክ እቅዳችን ሶስት የትምህርት ግቦችን ያስቀምጣል።የመጀመሪያው የመፃፍ ችሎታ በሶስተኛ ክፍል ይገነባል።በየWing Luke አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የንባብ ጉዟቸውን በቅርቡ አካፍለውናል። 

የ3ኛ ክፍል የንባብ ክህሎት ተማሪዎችን ለመለስተኛ ደረጃ ትምህርት ስኬታማነት ያዘጋጃቸዋል፣በዚህም ከጊዜ ወደ ጊዜ ውስብስብ የሂሳብ ትምህርት ጠንካራ የንባብ እና የፅሁፍ ችሎታዎች ይጠይቃል።የስትራቴጂክ እቅዳችን፣በአኪ ኩሮሴ መለስተኛ ደረጃ ት/ቤት እንደታየው የሂሳብ ክህሎትን እስከ 4ኛ ክፍል ማጠናከር ነው። 

ሦስተኛው የትምህርት ግብ የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ተመራቂዎች ለኮሌጅ እና ለስራ ዝግጁ መሆናቸውን ማረጋገጥ ነው።እና Ms. Wendy Miller እየተናገሩ ያሉት የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ጠንካራ የሂሳብ ችሎታዎች ተማሪዎችን ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ያዘጋጃሉ።ተማሪዎቻችን ልክ እንደ ሬኒየር ቢች ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሲያትል ለሚጠብቀው ነገር ዝግጁ ናቸው። 

ተልእኳችን አሳማኝ ነው።ስልታችን ግልፅ ነው።ጥቁር ወንዶች እና ወጣቶች ወደ የ3ኛ ክፍል የንባብ ብቃት፣ወደ የ7ኛ ክፍል የሒሳብ ብቃት እና ከሲያትል፣ወይም ሃዋርድ ወይም ሃርቫርድ እንዲመረቁ የሚያስችል የጸረ-ዘረኝነት የትምህርት ስርዓት እየገነባን ነው።ስለዚህ ጉዳይ በግሌ ለመናገር፣እኔ ከብዙ አመታት በፊት ያ ወጣት ነበርኩ እና ዛሬ በየቀኑ የምንታገልላቸው ብዙ ተማሪዎ ወጣቶች ናቸው። 

ይህንን እንዴት እንደምናደርግ እነሆ።የሚከተሉትን ለማድረግ ቃል ገብተናል:  

  • ለተማሪዎች እና ሰራተኞች ደህንነቱ የተጠበቀ እና ተቀባይ የሆነ የመማሪያ አካባቢዎችን ማቅረብ።  
  • የቀለም እና የትምህርት አጋሮች መምህራን መቅጠር፣ማቆየት እና ማሰልጠን  
  • በእያንዳንዱ ልጅ ስኬታማ የመሆን አቅም ላይ የአስተማሪዎችን እምነት የሚያዳብር ሙያዊ እድገትን መስጠት • ውጤታማ፣በጥናት ላይ የተመሰረተ የንባብ፣የፅሁፍ እና የቁጥር ትምህርት ሞዴሎች አስተማሪዎች ማሰልጠን 
  • 7ኛ ክፍል ለሚገቡ አፍሪካውያን አሜሪካውያን ወንዶች የሒሳብ ትምህርት እና ድጋፍ ጊዜ ማስፋት።  
  • የወላጆት የትምህርት ተሳትፎ የአካዳሚክ ስኬት በማምጣት ላይ በጣም ጠንካራው አመላካች መሆኑን ጥናቶች በተደጋጋሚ ስለሚያሳዩ፣ከቤተሰቦች ጋር ሁሉን አቀፍ እና ትክክለኛ ተሳትፎ ማሳደግ። 

የተማሪዎቻችንን ባህላዊ ማንነት እና የአካዳሚክ ብቃት-ብቃታቸውን እና የራስ መተማመን ማዳበር- ለማገዝ በት/ቤት ላይ በተመሰረቱ ስራዎች ላይ ኢንቨስት አድርገናል።በተጨማሪም፣ከመረጥናቸው የቢዝነስ፣የድርጅት እና የሲቪክ መሪዎቻችን ጋር ወሳኝ ውይይቶችን አድርገናል።የተማሪዎቻችን፣የቤተሰቦቻችን እና የሰራተኞቻችን ዋጋ እና ደህንነት በትምህርት ቤቶቻችን እና በአካባቢያችን በሚያጠናክሩ በተጨባጭ መንገዶች ላይ እጆቻችንን ለማሳረፍ ቃል ገብተናል። 

ሆን ብለን ድጋፋችንን በጣም ለሚፈልጉት ለማድረስ ኢላማ ካደረግን ሁለንተናዊ ስኬት እንደሚያስገኝ እናምናለን -የሁሉም የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የፅሁፍ/የንባብ፣የሂሳብ፣የኮሌጅ እና የሙያ ዝግጁነት። 

የ Nathan Hale ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመራር የታለመውን ሁለንተናዊነት ይገነዘባል። 

አሁን ከእቅድ ወደ ተግባባር የምንሸጋገርበት ጊዜ ነው።የትምህርት ቤቶቻችን ማህበረሰብ እና ደጋፊዎቻችንን በአጋርነት ጠረጴዛ ላይ ሲያትልን እንዲቀላቀሉ መጠየቅ እፈልጋለሁ:   

1. እንደ ማህበረሰብ፣የዲስትሪክቱ ስርዓቶችን የማሻሻል እና ተማሪዎቻችንን ከትምህርት ቤት ውጭ የመደገፍ እቅድ እናውጣ።    

2. ተማሪዎቻችን እንዲበለጽጉ የሚያስችሉ አጠቃላይ አካባቢ መፍጠር።  

3. የሲያትል ተማሪዎችን ስኬት ለመደገፍ በሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ውስጥ እና ውጭ ያሉትን ስርዓቶች ማጣጣም  

ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች የእኔ ብቻ ሳይሆን የእናንተም ቅርስ ነው።የት/ቤቶቻችን ቀጣይ ስኬት ከንቲባችን ካወጣው የሲያትል ስኬት አላማ አንዱ ነው።በሚቀጥሉት ወራት የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች መሪዎች እና ሰራተኞች በሚከተሉት መንገዶች ጠንክረው ሲሰሩ ታገኛላችሁ:  

  • ተማሪዎች እና የተማሪ ውጤቶች በእያንዳንዱ ውይይት እና በእያንዳንዱ ውሳኔ ማእከል የሚያደርግ አስተዳደር ተግባራዊ ለማድረግ ከትምህርት ቦርድ ጋር መስራት  
  • ጊዜያችን፣ችሎታችን እና ሀብታችን በ3ኛ ክፍል ንባብ፣በ7ኛ ክፍል ሂሳብ እና የኮሌጅ እና የሙያ ዝግጁነት ኢንቨስት ማድረግ። ““Seattle Ready”” በትክክል ምን ማለት እንደሆነ ለአለም የሚያሳዩ ተማሪዎችን እያስመረቅን ነው።  
  • ከሲያትል ከተማ ጋር ያለንን አጋርነት ማሳደስ፣የሚከተሉት ጨምሮ:  
  • የከንቲባ ቢሮ፣የትምህርት እና የቅድመ መደበኛ ትምህርት ዲፓርትመንት፣የሲያትል ፖሊስ ዲፓርትመንት እና እንደ የንግድ ምክር ቤት አጋሮቻችን ያሉ የሲያትል የንግድ ማህበረሰብ፣እና የሲያትል ኮሌጆች፣የዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ፣ የሲያትል ዩኒቨርሲቲ እና የሌሎች የከፍተኛ ትምህርት አጋሮች። 
  • የፊስካል ሃላፊነትን ማሳየት እና አዲስ የፀደቀውን የቀረጥ ስራዎች ማሟላት።ወደ 80% የሚጠጋው የማህበረሰባችን ክፍል – የሲያትል መራጮች – ለረዥም ጊዜ ዘላቂነታችን የትምህርት ቤት ክፍያዎች አዎ አሉ። በትምህርት ቤቶቻችን ላይ ያለዎት እምነት እና ተስፋ በጣም አስደናቂ ነበር እናም የገባነውን ቃል እንፈጽማለን። 

ከንቲባ Harrell ተማሪዎችን ከቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ወደ Seattle Promise ለመውሰድ ከእኛ ጋር እየሰራ ነው። 

ለወጣቶቻችን የሚበጀውን እናድርግ።የበለጠ ታማኝ የህዝብ ትምህርት ቤት እንሁን።የንግድ እና የሲቪክ ማህበረሰብ እና ሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎቻችን ባህላዊ ድጋፍ፣አካላዊ እና ስሜታዊ ደህንነት፣ከፍተኛ ተስፋዎች እና ብዙ ዕድሎች ለመስጠት ቃል ኪዳን ገብተዋል።  

ሁሌም በሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች እና በተማሪዎቻችን ስለምንተማመን እናመሰግናለን።በእርስዎ ድጋፍ ምክንያት፣አዲስ የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን በተሻለ ለማገልገል፣ተመራቂዎች ለኮሌጅ፣ለስራ እና ለህይወት ዝግጁ ሆነው እንዲመረቁ በማድረግ ይህን አመት በጥንካሬ ለመጨረስ ተዘጋጅተናል።እያንዳንዱን የትምህርት ቀን እና እያንዳንዱን የትምህርት አመት ግምት ውስጥ ማስገባት አለብን።ተማሪዎቻችን በተለይም ከትምህርታዊ ፍትህ በጣም ርቀው የሚገኙ የቀለም ተማሪዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ አሁን ይፈልጉናል።አንድ ላይ ሆነው ስኬታማ መሆናቸውን ማረጋገጥ እንደምንችል አምናለሁ።  

በዚህ ምሽት ከኛ ጋር ስለተገኛቹ እናመሰግናለን።ደህና ሁኑ!