Seattle Public Schools

Resources

Student Meals

የተማሪ ምግቦች

የምግብዓይነቶች(Menus)

የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በእያንዳንዱ የትምህርት ቀን ሶስት የምግብ አማራጮች ይሰጣቸዋል (አንድ ሙቅ እና ሁለት ቀዝቃዛ)።

ለተማሪዎችነፃምግብ

ልጅዎ ለነጻ ወይም ለቅናሽ ምግብ ብቁ ሊሆን ይችላል።በሁሉም የሲያትል ትምህርት ቤቶች፣ለነጻ ወይም ለቅናሽ ዋጋ ምግብ ብቁ የሆኑ ተማሪዎች ያለ ምንም ወጪ ምግብ ያገኛሉ።

በየዓመቱ እንደገና ማመልከት አለብዎት።ብቃት በቤተሰብ ገቢ ላይ የተመሰረተ ነው።

ለዚሁ ፕሮግራም ብቁ የሆኑ ተማሪዎች ለሚከተሉት ፕሮግራሞች የቅናሽ ክፍያን ጨምሮ ተጨማሪ ጥቅማጥቅሞችን ያገኛሉ።

  • የዝግጅት ክፍያዎች
  • የመስክ ጉዞዎች
  • የላቀ ፕሮግራም የምደባ ፈተናዎች
  • የRunning Start መጽሐፍት
  • የAssociated Student Body (ASB) ክፍያዎች
  • የቅድመ-ኮሌጅ ፈተናዎች (PSAT/SAT/ACT)
  • የኮሌጅ ማመልከቻ ክፍያዎች

የነፃ እና የቅናሽ ዋጋ ምግቦች ማምልከቻ

ደህንነቱ በተጠበቀ የመስመር ላይ ቅፅ ለነጻ እና ለቅናሽ ምግቦች ማመልከት ይችላሉ።የሚቀጥለው ዓመት ማመልከቻዎች በነሐሴ ወር ይገኛሉ።ማመልከቻዎ ከታየ በኋላ፣ልጅዎ ብቁ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ ይደርስዎታል።

ከዚህ በታች ባለው ዝርዝር የቤተሰብዎን ብዛት ይመልከቱ።ገቢዎ ለቤተሰብዎ ብዛት ከተገለፀው ገቢ ያነሰ ከሆነ፣ለምግብ ጥቅማጥቅሞች ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ እና ማመልከቻውን መሙላት አለብዎት።

ለነጻ እና ቅናሽ ምግብ ብቁ ከመሆዎ በፊት ለሚኖር የተማሪው ምግብ ወጪ ቤተሰቦች ሃላፊነት ይወስዳሉ።

ተደጋግመውየሚነሱጥያቄዎች

ለልጄ ለነጻ ወይም ለቅናሽ ዋጋ ምግብ እንዴት ማመልከት እችላለሁ?

የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች የምግብ አገልግሎቶች፣የተማሪን ብቁነት ለመወሰን የመስመር ላይ ማመልከቻ ወይም የወረቀት ማመልከቻ ይጠቀማል።

ለነጻ ወይም ለቅናሽ ምግብ ብቁ የሆኑ ተማሪዎች በሁሉም የሲያትል ትምህርት ቤቶች ያለ ምንም ክፍያ ምግብ ያገኛሉ።

ማመልከቻው ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ በየዓመቱ ለቤተሰቦች ዝግጁ ይሆናል።የምግብ ጥቅማ ጥቅም ማመልከቻዎች እንዲታዩ ከ7-10 ቀናት ሊወስድ ይችላል።

የተማሪዎ ብቁነት በትምህርት አመቱ መጀመሪያ ላይ መመዝገቡን ለማረጋገጥ እባክዎ የአመቱን ማመልከቻ በተቻለ ፍጥነት ይሙሉ።

ማመልከቻውን በየዓመቱ ማመልከት አለብዎት።

ልጄ ለዚሁ ብቁ መሆኑን እንዴት አውቃለሁ?

ሂደቱ እንደተጠናቀቀ፣ቤተሰቦች የተማሪውን ብቁነት የሚገልፅ ደብዳቤ በፖስታ ይላክላቸዋል።

እባክዎን ይህንን ደብዳቤ ለየትምህርት ቤት የመስክ ጉዞ፣የአትሌቲክስ ወይም የፈተና ክፍያዎች ቅናሽ ያስቀምጡ።ድጋሚ ደብዳቤ የሚያስፈልጋቸው ቤተሰቦች የምግብ አገልግሎቶችን በስልክ ቁጥር 206-252-0675 ማግኘት ይችላሉ።

ልጄ ልዩ የምግብ ፍላጎት አለው።የትምህርት ቤት ምግብ ያገኛል?

አዎ።ትክክለኛ ምግቦች ለልጅዎ መኖራቸውን ለማረጋገጥ እባክዎን የምግብ ማዘዣ ቅጽ ያቅርቡ።

የምግብ ማዘዣ ቅጾችን(Diet Prescription )ያውርዱ።እንዲሁም የምግብ አገልግሎቶችን በ 206-252-0675 በማግኘት ቅጾችን ሊጠየቁ ይችላሉ።

የተጠናቀቁ ቅጾችን ወደ የትምህርት ቤቱ የምሳ ክፍል መውሰድ ወይም ወደሚከተለው በፖስታ መላክ ይችላሉ:

Seattle Public Schools Culinary Services
MS 32-372
P.O. Box 34165
Seattle, WA 98124