Seattle Public Schools

School Lunch and Breakfast

Summary: ቁርስ እና ምሳ በነፃ ወይም የምግብ ዋጋ መጉደል እንዲደረግላቸ ኣመልክተው ለተቀበልናቸው ተማሪዎች በነፃ ይሰጣል።

ብሔራዊ የትምህርት ቤት ምሳ ፕሮራም/ ብሔራዊ የትምህርት ቤት ቁርስ ፕሮግራም

የተከበራችሁ ወላጆች/ኣሳዳጊዎች፡
ይህ መልእክት ልጆቻችሁ ትምህርት ቤት ኣንዴት በነፃ ወይም የምግብ ዋጋ ቅናሽ ሊደረግላቸው እንደሚችል መረጃ እና ሌላ ተጨማሪ መረጃ ስለ ሌሎች እርዳታዎች (ቤነፊት) የሚሰጥ ነው። ትምህርት ቤቶች ስለ
ሚያያዘጋጁት ምግብ ዋጋ ዝርዝር ከዚህ በታች ይመልከቱ።

መደበኛ ዋጋ

ቁርስ እና ምሳ በነፃ ወይም የምግብ ዋጋ መጉደል እንዲደረግላቸ ኣመልክተው ለተቀበልናቸው ተማሪዎች በነፃ ይሰጣል። የተቀሩት ሌሎች ተማሪዎች በሚከተለው መሰረት ይከፍላሉ።

ኣንደኛ ደረጃ (ኢለመንታሪ) / K-8

  • ቁርስ $2.25
  • ምሳ $3.25

መሃከለኛ ደረጃ / ሁለተኛ (ሃይ ስኩል)

  • ቁርስ $2.50
  • ምሳ $3.50

ይህን የማመልከቻ ፎርም ማን መሙላት ይገባዋል?

የሚከተሉትን መመዘኛዎች የምታሟሉ ከሆኑ ይህን ፎርም ይምሉ:

  • ዓመታዊ የቤተሰብ ገቢያችሁ እታች ሳጥኑ ውስጥ ከተዘረዘረው መጠን እኩም ወይም በታች ከሆነ፡
  • ለልጆችዎ ቤዚክ ፉድ፣ ለኢንዲያን ረሰርቬሽንስ የሚደረግ የምግብ ማከፋፈል ፕሮግራም (FDPIR) ወይም ግዝያዊ እርዳታ ለተቸገሩ ቤተሰቦች (TANF) የሚቀበሉ ከሆኑ፡
  • ለማደጎነት በሃላፊነት በሚያሳድግ ድርጅት ስር ወይም በፍ/ቤት ስር ለሚገኙ የማደጎ ልጆች የሚያመለክቱ ከሆነ

ኣንድ የማመልከቻ ፎርም ለኣንድ ቤተሰብ መሙላታችሁን ኣረጋግጡ። ማመልከቻችሁን እንደተቀበልነው ወይም እንዳልተቀበልነው በጊዜ እናሳውቃቹህ ኣለን። የሚያመለክቱለት ያሉት ልጅ
የጎደና ተዳዳሪ ከሆነ (ማክኔይ-ቢንቶ) ወይም ስደተኛ ከሆነ የሚመለከትው ሳጥን ውስጥ ምልክት ያድርጉ።.

ይህን የማመልከቻ ፎርም ምልተው ወደ የትምህርት ቤትዎ የምግብ አገልግሎት ያድርሱት ወይም በፖስታ ቤት በኩል በሚከተለው ኣድራሻ ወደኛ ይላኩት: Culinary Services – MS32-372; PO Box 34165 Seattle, WA 98124 ; ወይም ለምግብ አገልግሎት በፋክስ ቁጥር 206-252-0664 ይላኩ; ወይም በኢሜል culinaryservices@seattleschools.org ይላኩ::

የማመልከቻ

የቤተሰብ ገቢ ምን ያጠቃልላል? ማን ነው ኣንደ ቤተሰብ ኣባል የሚቆጠረው?

እታች ያለውን የገቢ ቻርት ተመልከቱ። የቤተሰብዎን ቁጥር ያግኙ። ከቤተሰብዎ ቁጥር ጋር የሚስማማውን ጠቅላላ ገቢ ይመልከቱ። የቤተሰብዎ ኣባላት ደሞዝ በወሩ ውስጥ በተለያየ ግዜ የሚከፈሉ ከሆኑ እና
ቤተሰብዎን ብቁ መሆኑ እና ኣለመሆኑ እርግጠኛ ካልሆኑ፤ ይህን ፎርም ዝም ብለው ይምሉት፣ እኛ በገቢዎ መሰረት ለዚህ እርዳት የሚበቁ እንደሆኑ እና እንዳልሆኑ እንወስናለን። ይህ የምትሰጡት መረጃ ልጆቻችሁ
ለነፃ ወይም የዋጋ ቅናሽ የተደረገለት ምግብ ብቁ መሆናቸውን እና ኣለመሆናቸውን እንድንወስን ያግዘናል።

የማደጎ ልጆች በአሳዳጊው ድርጅት ወይም ፍርድ ቤት ሃላፊነት ስር ሆነው ምንም ዓይነት የግል ገቢ ሳይታይ ለነጻ ምግብ ብቁ ይሆናሉ:: ስለ ለማደጎ ልጆች የሚሰጥ ነፃ ምግብ የሚመለከት ጥያቄ ካላዎ
እባክዎ በሚከተለው የስልክ ቁጥር ደውለው ያነጋግሩን 206-252-0675

ቤተሰብ ማለት እዚህ ጽሑፍ ውስጥ የሚከተለውን ይወክላል፤ ወላጆች፣ ልጆቻቸው፣ ኣያቶች እና ዘመድ ይሁኑ ኣይሁኑ እቤታችሁ የሚኖሩ ወይም ወጪዎቻችሁን የሚያካፍሉዋችሁ ያጠቃልላል። ማመልከቻችሁ ላይ የማደጎ ልጅ የሚያሳድ ቤተሰብ ብላችሁ እያመለከታችሁ ከሆነ፤ የማደጎ ልጅዎን ጠቅላላ የቤተስብ ብዛት ውስጥ ሊያስገቡት ይችላሉ።

የቤተሰብ ገቢ ማለት ድምር ገቢ የሁሉም የቤተሰብ ኣባሎች ከታክስ በፊት ያጠቃልላል። ይህ ደሞዝ፣
ሶሻል ሴኩሪቲ፣ ጡረታ፤ ኣንኢንፕሎይመንት፣ ዌልፌር፣ ለልጅ የሚሰጥ እርዳታ፣ በፍርድ ቤት የተወሰነ
የልጅ ማሳደጊያ ገንዘብ እና ሌላ የሆነ ገቢ የገንዘብ ገቢ ያጠቃልላል። የማደጎ ልጅ እዚህ ማመልከቻ ውስጥ
እንደ ቤተሰብ ኣባል ካስገባችሁት፤ የማደጎ ልጅዎን ገቢ የቤተሰብ ጠቅላላ ገቢ ውስጥ ያስገቡት። ለማደጎ
ልጅ የሚሰጥ ልዩ ክፍያ ጠቅላላ ገቢ ውስጥ ሪፖርት ኣታድርጉት።

የገቢ ቻርት

የቤተሰብ
ብዛት
የዓመትየወር2 x የወርበ2 ሳምንትበሳምንት
1$25,142$2,096$1048$967$484
2$33,874$2,823$1,412$1,303$652
3$42,606$3,551$1,776$1,639$820
4$51,338$4,279$2,140$1,975$988
5$60,070$5,006$2,503$2,311$1,156
6$68,802$5,734$2,867$2,647$1,324
7$77,534$6,462$3,231$2,983$1,492
8$86,266$7,189$3,595$3,318$1,659
ሌላ ተጨማሪ የቤተሰብ
ኣባል ካለ የሚከተለውን
መጠን ለኣንድ ሰው ደምሩበት::
+ $8,732+ $728+ $364+ $336+ $168