Seattle Public Schools

Resources

Attendance

ማስታወሻ: ከተማሪዎ አቴንዳንስ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች ካሉዎት እባክዎን ትምህርት ቤትዎን ያነጋግሩ።. 

የአቴንዳንስ ፖሊሲ 

ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ለትምህርት ስኬት በጣም ወሳኝ ከሆኑት ትንበያዎች አንዱ አቴንዳንስ መሆኑን እና ተማሪዎ በትምህርት ገበታው ከተገኘ እና በእያንዳንዱን የትምህርት ቀን ለመማር ዝግጁ ከሆነ፣ለእሱ፣ለክፍል ጓደኞቹ እና ለመላው የትምህርት ቤት ማህበረሰብ ይጠቅማል ብሎ ያምናል።በዚህ የትምህርት ዓመት ተማሪዎ ከፍተኛ አቴንዳንስ እንዲኖረው ለማረጋገጥ እባክዎን ያግዙን። 

ከኛ የሚጠበቅ ነገር 

ተማሪዎች ከጤና እክሎች ጀምሮ እስከ የትራንስፖርት ችግሮች ከትምህርት ገበታ የሚቀሩባቸው የተለያዩ ምክንያቶች እንዳሉ እናውቃለን።ተማሪዎ ትምህርቱን በመደበኛነት ለመከታተል ወይም በሰዓቱ ለመገኘት ችግሮች ካጋጠሙዎት በሕንፃዎቻችን ውስጥ እርስዎን ለመርዳት የተዘጋጁ ብዙ ሰዎች አሉ።ተማሪዎ በአካልም ሆነ በርቀት ትምህርቱን እንዲከታተል በየቀኑ አቴንዳንስ ለመከታተል፣ተማሪዎ ከትምህርት ሲቀር ለማሳወቅ፣ለምን እንደቀረ ለመረዳት ከእርስዎ ጋር ለመነጋገር እና ተማሪዎ ትምህርቱን እንዳይከታተል ሊያጋጥሙዎት የሚችሉትን ፈተናዎች ለማሸነፍ ያሉትን መሰናክሎች እና ድጋፎች በመለየት ላይ ለማገዝ እንሰራለን። 

ከእርስዎ የምንፈልገው 

 ተማሪዎ ከትምህርት ሲቀሩ እንናፍቃችዋለን እንዲሁም ለት/ቤታቸው የሚያደርጉትን አስተዋፅኦ ዋጋ እንሰጣለን። ተማሪዎ በአካልም ሆነ በርቀት ሲማር፣ትምህርቱ በመደበኛነት እንዲከታተል እና በትምህርቱ ስኬታማ እንዲሆን እንዲያግዙን እንፈልጋለን።ተማሪዎ ከትምህርት የሚቀር ከሆነ፣እባክዎን የተማሪዎን ትምህርት ቤት አስቀድመው ያሳውቁ።ተማሪዎ ባልታቀደ ሁኔታ የሚቀር ከሆነ በተመለሰ በሁለት የትምህርት ቀናት ውስጥ እባክዎን ትምህርት ቤቱን ያሳውቁ። 

ለማገዝ ምን ማድረግ ይችላሉ 

ልጅዎ የበአካል ትምህርት የሚማር ከሆነ 

  • በ WAC 392-401-020 በተገለጸው መሠረት እንደ ትኩሳት፣ማስታወክ፣ተቅማጥ፣ተላላፊ ሽፍታ፣ወይም ከ ኮቪድ-19 ጋር የተዛመዱ ማንኛውም የጤና ሁኔታዎች ካሉት እና በትክክል ካልታመመ በስተቀር ትምህርቱን እንዲከታተል ያድርጉ። 
  • ጉዞዎች እና ቀጠሮዎች ሲያቅዱ ከትምህርት ጊዜ ውጭ ያድርጉ። 
  • የልጅዎን አቴንዳንስ ይከታተሉ።ልጅዎ ምክንያታዊ በሆነ ወይም ምክንያታዊ ባልሆነ ነገር ከትምህርት ሲቀር በትምህርቱ ወደ ኋላ ሊያስቀረው ይችላል። 
  • መደበኛ የሆነ የመኝታ ሰዓት እና ጠዋት ከመኝታ የሚነሱበት ሰኣት ያቅዱ። ልጅዎ የቤት ሥራውን ከመተኛቱ በፊት ማጠናቀቁን ያረጋግጡ። 

ልጅዎ የርቀት ትምህርት የሚማር ከሆነ 

  • ልጅዎ ወደተመደበለት የመስመር ላይ(የርቀት) ስብሰባዎች እና ትምህርቶች እንዲገባ ያድርጉ እና ልጅዎ በግል የሚሰሩ የትምህርት ስራዎችን ማግኘት መቻሉን ያረጋግጡ።ስለ የርቀት ትምህርት አቴንዳንስ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣እባክዎን WAC 392-401-016.ን ይመልከቱ። 
  • እንደ ትኩሳት፣ማስታወክ፣ተቅማጥ፣ወይም ከኮቪድ-19 ጋር የተተያያዙ ማንኛውም የጤና ሁኔታ ምክንያት ተማሪዎ የመስመር ላይ(የርቀት) ስብሰባዎች ወይም ትምህርቶች ወይም በግል የሚሰሩ የትምህርት ስራዎችን የማይሳተፍ ከሆነ እባክዎን የልጅዎን ትምህርት ቤት ያሳውቁ። 
  • ተጨማሪ ድጋፍ ካስፈለገ ወይም ተማሪዎ በየርቀት ስብሰባዎች ፣ትምህርቶች ወይም የትምህርት ስራዎች እንዳይሳተፍ የሚያግዱ እንቅፋቶች ካሉ ለመወያየት የልጅዎ ትምህርት ቤት እና አስተማሪ ያነጋግሩ። 
  • መደበኛ የሆነ የርቀት ትምህርት እቅድ ያውጡ። ልጅዎ ከመተኛቱ በፊት የትምህርት ስራዎችን ማጠናቀቁ ያረጋግጡ። 

የዚህ ደብዳቤ ክፍሎች ለየአቴንዳንስ ሥራዎች ተጠቃሾች ናቸው 

የዲስትሪክቱ መገኛዎችን ጨምሮ ተጨማሪ የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች አቴንዳንስ መረጃ በ www.seattleschools.org/attendance ላይ ሊገኝ ይችላል።