Seattle Public Schools

በታቀዱት የደወል ጊዜ ለውጦች ዝመናዎች

Summary: እነዚያን ተግዳሮቶች ለመፍታት ብዙ ጊዜ እየወሰድን ነው።

የታቀዱት የትምህርት ቤት የመጀመሪያ ሰአታት (የደወል ሰአታት)ለውጦች እንደተጠበቀው በሚያዝያ 4 በነበረው የትምህርት ቦርድ ስብሰባ ላይ አልቀረቡም።

ይህ የታቀደው ለውጥ ለቤተሰቦች እና ሰራተኞች ሊፈጥረው ስለሚችል ችግር ከቤተሰቦቻችን እና ከማህበረሰብ አጋሮቻችን ብዙ አስተያየቶችን ተቀብለናል።እነዚያን ተግዳሮቶች ለመፍታት ብዙ ጊዜ እየወሰድን ነው።

ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን በሰዓቱ ወደ ትምህርት ቤት የሚያደርስ እና ለመማር ዝግጁ የሚያደርግ አስተማማኝ ትራንስፖርት ለማቅረብ ቁርጠኛ ነው።ይህንን እቅድ ስንገመግም፣ሰራተኞች በሚቀጥሉት በርካታ ሳምንታት ከትምህርት ቤቶች፣ቤተሰቦች እና አጋሮች ጋር መስራታቸውን ይቀጥላሉ።እኛም ወቅታዊ መረጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ለቤተሰቦች ማሳወቅ እንቀጥላለን።

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎችን ጨምሮ ወቅታዊ መረጃዎችን በየደወል ጊዜ ድረ-ገጽ( bell times webpage)ላይ ማግኘት ይችላሉ።

ስለታቀዱት ለውጦች አስመልክቶ በእንነጋገር አገናኝ(Let’s Talk link )እንዲሁም በሌሎች ዘዴዎች ላገኛሁን ሁሉ እናመሰግናለን።ሁሉንም ግብረመልሶች መገምገማችንን እንቀጥላለን እንዲሁም ከሰራተኞች እና ከትምህርት ቤት ቦርድ ዳይሬክተሮች ጋር እናጋራለን።አስተያየቶችዎን እና ስጋቶችዎን ለማጋራት የተሻለውን መንገድ እንነጋገር(Let’s Talk) ነው።

You may also be interested in

የትምህርት የመጀመሪያ ሰዓት ለውጥ ፕሮፖዛል 2022-23

ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (SPS) የቀጣዩ የትምህርት ዓመት የደወል ጊዜ (የትምህርት መጀመሪያ እና መጨረሻ ጊዜ) እንዲቀየር ሐሳብ አቅርቧል።…
A graphic with clock and bell

በ2022-23 የትምህርት ዓመት የትምህርት መጀመርያ ሰዓት የደረገ ለውጥ የለም

ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ሰዓት ለመቀየር የቀረበው ሃሳብ አስመልክቶ ከብዙ ቤተሰቦች ስጋቶችን ሰምተናል።…
A graphic with clock and bell

ስለ 2022-23 የታቀዱ የደውል ጊዜያት ተጨማሪ መረጃ ያግኙ

Seattle Public Schools ከመስከረም 2022 ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የትምህርት መጀመሪያ ሠዓት ለውጥ ለማድረግ አቅዷል።…