Main navigation

Resources

Preschool and Kindergarten

Seattle Public Schools Preschool and Kindergarten Information

Headstart

የሚከተሉትን አገልግሎቶች እንሰጣለን::

 • የግማሽ ቀን እና በተወሰኑ ቀናት የሙሉ ቀን ፕሮግራሞችን በሲያትል በሚገኙ የ1ኛ ደረጃ ት/ቤቶች እንሰጣለን!!
 • የቤት ለቤት ትራንስፖርት አገልግሎት
 • የተለያየ ችሎታ ያላቸውን ልጆች የሚያካትት የመማሪያ ክፍል
 • ለመደበኛ ት/የሚያዘጋጅና የኪንደርጋርተን/አጸደ ህጻናት/ሽግግር
 • የቤተሰብ ድጋፍ አገልግሎት
 • ምግብ ተካቷል

የምናገለግላቸው:

 • እድሜያቸው ነሃሴ 31 ላይ 4 ወይም 3 የሞላቸው::
 • ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል
 • ከስራ ጋር በተያያዘ ከዲኤስ ኤች ድጋፍ/ TANF/የሚያገኙ ቤተሰቦች
 • ቤት የሌላቸውና ማደጎ ህጻናት ወዲያውኑ ለፕሮግራሙ ብቁ ይሆናሉ!

Early Learning Department 206-252-0960


Preparing for Kindergarten

Helping Your Child Prepare for Kindergarten

ወላጆች እና ቤተሰብ የልጃቸው የመጀመሪያ መማህራን እንደመሆነቸው መጠን በህጻናት ትምህርት ላይ ትልቅ ተራ ይጫወታሉ። ልጆች በተለያየ መልክ እና ደረጃ ትምህርት ይቀስማሉ። ወደ ትምህርት ቤትም ሲመጡ የተለያየ ችሎታ ይዘው ነው የሚመጡት። እነዚህ መመሪያዎች ተማሪዎች ለመዋለ ህፃናት ለመዘጋጀት የሚያስፈልጓቸውን ስድስት የእድገት ዘርፎችን ላይ ያተኩራሉ። ቀጥሎ የቀረበው ዝርዝር ከልጅዎን ጋር እሱ/እሷን በይበልጥ ለመዋለ ህፃናት ለማዘጋጀት ማድረግ ያለብዎን ኣንዳንድ ዝግጅቶች እና ዘዴዎች ይጦቅማል

ማህበራዊ / ስሜታዊ

 • ልጄባለ 2-ደረጃመመሪያዎችንሁሌየስማል(ይከተላል)በተጨማሪምባል 3-ደረጃመመሪያዎችንመማርእየጀመረነው።
 • ልጄእለታዊተግባራትንያስታውሳልዘውትርይከተላል (ለምሳሌ፤እራት፣ገላውንመታጠብ፣ጥርሱንማጽዳት፣ለመኝታግዜትረካይዘጋጃል፣ወደመኝታይሄዳል)።
 • ልጄስሜቱንመግለጽ (ለምሳሌ፤ደስብሎኛል፣ኣዝኛለሁ፣ዛሬተነሳስቻለሁ)ይችላል።
 • ልጄሲጨነቅወይሲቆጣእራሱ/ራሷንመቆጣጠርይችላል።
 • ልጄየራሱን/የረሷንኮትመልበስይችላል/ትችላለች።
 • ልጄሽንትቤትያለምንምእርዳታመጥቀምይችላል/ትችላለች።
 • ልጄእጁን/እጇንመታጠብይችላል/ትችላለች።                           
 • ልጄመጫወቻውንበስነስርዓትማስቀመጥ፣ትንንሽየፈሰሰነገርማጽዳትእናየተጠመበትንነገርቦታውመመለስይችላል/ትችላለች።
 • ልጄለሌሎችማካፈል፣ተራመጠበቅእናሌሎችንማግዝይችላል/ትችላለች።
 • ልጄኣዲስነገርወይም/እናኣዲስስዎችጋርመላመድይችላል/ትችላለች።
 • ልጄከሌሎችጋርተስማምቶመጫወትይችላል/ትችላለች።
 • ልጄሌሎችንማጽናናትይችላል/ትችላለች።
 • ልጄበራሱ/በራሷዕድሜክልልካሉየተለመዱጓደኞችጋርሁሌምየመየጫወትዕድልኣግኝቷል/ኣግኝታለች

ኣካላዊ

 • ልጄመሮጥ፣መዝለልእናመጋለብይችላል/ትችላለች።
 • ልጄበኣንድእግሩመቆምይችላል/ትችላለች።
 • ልጄትልቅኳስመቅለብእናመወርወርይችላል/ትችላለች።
 • ልጄኳስመምታትይችላል/ትችላለች።
 • ልጄበመቀስመቁረጥይችላል/ትችላለች።
 • ልጄእርሳስመያዝእናመጠቀምይችላል/ትችላለች።.
 • ልጄመታጠቅ፣ዚፕመዝጋት፣መቀንጠስእናቁልፉመቆለፍይችላል/ትችላለች

ቋንቋ

 • ልጄየራሱን/ያረሷንሃሳብእናፍላጎትለመግለጽቃላትይጠቀማል/ትጠቀማለች።
 • ልጄበራሱ/በራሷቃላትተጠቅሞ/ተጠቅማየተለመዱነገሮችመግለጽእናመሰየምይችላል/ትችላለች።.
 • ልጄበየቀኑኣዳዲስቃላትይጠቀማል/ትጠቀማለች።
 • ልጄኣጥርቶይናገራልበተጨማሪምሲናገር/ስትናገርኣብዛኛዎቹሰዎችንግግሩ/ሯይገባቸዋል።
 • ልጄከ4ኣስከ 6ቃላትያለውኣርፍተነገርይናገራል።
 • ልጄባለፈግዜስላጋጠመነገርበዝርዝርመናገርትችላለች/ይችላል።
 • ልጄስለኣንድኣርእስትከሌላሰውጋርተራውንእየጠበቀመነጋገርይችላል/ትችላለች

የኣእምሮ እድገት

 • ልጄችግርለመፍታትከኣንድበላይመንገዶችማሰብይችላል/ትችላለች።
 • ልጄጥያቄዎችንለመመለስጉጉትእናፍላጎትኣለው/ኣላት።
 • ልጄችግርመፍታትእናጨወታላይተጣጣፊነትእናፈጣሪነትያሳያል/ታሳያለች።
 • ልጄነገሮችንበቀለማቸው፣በቅርጻቸውወይምመጠናቸውመመደብይችላል/ትችላለች።
 • ልጄጸጥብሎመቀመጥ፣ነቅቶእናየያዘውነገርላይኣተኩሮመቆየትይችላል/ትችላለች

ማንበብ እና መጻፍ

 • ልጄከ5እስከ 10ቤትየሚመቱቃላትንመለየትወይምየህጻናትመዝሙርመዘመርይችላል/ትችላለች።
 • ልጄቃላትበተመሳሳይድምጽመጀመራቸውን (ለምሳሌ፤ቢግ፣ብራውን፣ቢር)መለየትይችላል/ትችላለች።
 • ልጄያንድየሆነቃልክፍሎችን (ለምሳሌ፤ሃ–ፒ (hap-py)ባለ 2ክፍልእና 2ኣናባቢ)መስማትይችላል/ትችላለች።
 • ልጄከ10እስከ 20በትልቁእናከ10እስከ 20በትንሹየተጻፉፊደላትንመለየትእናመጥራትይችላል/ትችላለች።
 • ልጄከ10እስከ 20የሚደርሱፊደላትበትክክልማድመጽይችላል/ትችላለች።
 • ልጄየመጽሓፍኣካላትንለምሳሌሽፋን፣ኣርእስት፣ገጽ፣ቃላትወዘተ…ያውቃል/ታውቃለች።
 • ልጄከኣዋቂጋርያነባልበተአጨማሪምተረትተረትምያዳምጣል።ስለሰማውታሪክመናጋርእናየሰማንታሪክደግሞመተረክይችላል/ትችላለች።
 • ልጄታረካ/ተረትስእልበመሳልወይም/እናበጽሓፍመጻፍይችላል/ትችላለች።
 • ልጄስሙንመጻፍእናየስሙን/የስሟንፊደላትይለያል/ትለያለች።
 • ልጄፊደላትንመለየትይችላል

ሂሳብ

 • ልጄከ10እስከ 20የሚሆኑነገሮችንእየጦቀመመቁጠርይችላል/ትችላለች።
 • ልጄእስከ 20በተርታጭክብሎመቁጠርይችላል/ትችላለች።
 • ልጄይበልጣል፣ያንሳልወይምእኩልነውየሚሉትንቃላትመረዳትጀምሯል/ጀምራለች።
 • ልጄከ1እስከ 10ያሉቁጥሮችንመለየትይችላል።
 • ልጄከ1እስከ 10ያሉቁጥሮችንተማሳሳይቁጥርካላቸውነገሮችጋርማዛመድይችላል/ትችላለች።
 • ልጄየተለመዱቅርጾችንለምሳሌ፤ክብ፣ኣራትመኣዝን፣ሦሥትመኣዝንወዘተ…መለየትይችላል/ትችላለች።
 • ልጄየተለመዱቀላልቅርጾችንማዛመድእናመለያየትይችላል/ትችላለች።
 • ልጄሲጫወትመለኪያዎችለምሳሌ፡ኩባያ፣ማንኪያ፣ማስመሪያ፣ሚዛንወዘተ…ይጠቀማል/ትጠቀማለች።
 • ልጄቃላትበመጠቀምነገሮችንበመጠን፣በቅርጽእናክብደትለምሳሌ፤ትልቅ፣ክብ፣ከባድወዘተ…ይገልጻል/ትገልጻለች።
 • ልጄነገሮችንበቅደምተከተልማስቀመጥለምሳሌ፤ 1ደኛ፣ 2ተኛ፣ 3ተኛወዘተ…ይችላል/ትችላለች

የግል መረጃ

 • ልጄስሙን/ስሟን፣ያባቱን/ያባቷንስምእናየቤተሰቡን/የቤተሰቧንስምያውቃል/ታውቃለች።
 • ልጄየራሱን/ያረሷንኣድራሻእናስልክቁጥርያውቃል/ታውቃለች።
 • ልጄእስከ 10የሚደርሱየሰውነትክፍሎችን (እራስ፣ትከሻ፣ቁርጭምጭሚት፣እጣትወዘተ…)መጥራትይችላል/ትችላለች።
 • ልጄእድሜውንእናየልደትቀኑንያውቃል/ታውቃለች

የኪንደርጋርተን ትምህርት የሚጀምረው ከ ጃምፕ ስታርት ነው 

ከነሃሴ 15-19, 2022 ከ 9am -12 እኩለ ቀን 

በተመደቡበት ትምህርት ቤት ከግንቦት ወር ጀምሮ 

ለ ጃምፕ ስታርት ይመዝገቡ 

ጃምፕ ስታርት ምንድን ነው? 

ጃምፕ ስታርት የኪንደርጋርተን ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው የሲያትል ትምህርት ቤቶች ልምድ እንዲያገኙ በነጻ የሚሰጥ የአንድ ሳምንት ፕሮግራም ነው።ልጆች ከትምህርት ከጓደኞቻቸው እና ከትምህርት ቤት ሰራተኞች ጋር ይገናኛሉ እና ከትምህርት ቤቱ ጋር ይተዋወቃሉ ፡፡ግባችን አዳዲስ የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች የኪንደርጋርተን ተማሪዎች ደህንነት እንዲሰማቸው፣ድጋፍ እንዲያገኙ እና ለመማር ዝግጁ እንዲሆኑ ማድረግ ነው። 

 ጃምፕ ስታርት የት ይሰጣል? 

አብዛኛዎቹ የሲያትል አንደኛ ደረጃና K-8 ት/ቤቶች የጃምፕ ስታርት ፕሮግራም ይሰጣሉ።ትምህርት ቤትዎን ይህንን ፕሮግራም የሚሰጥ ከሆነ ለማወቅ እባክዎን ትምህርት ቤትዎን ይጠይቁ። ልጆች ጃምፕ ስታርትን ለመከታተል ፕሮግራሙን በሚሰጡ(በተጠባባቂ ላይ ያሉ ሳይሆኑ) ት/ቤቶች መመደብ አለባቸው።ትምህርት ቤቶች ለእንግሊዝኛ ቋንቋ ተማሪዎች የቋንቋ ድጋፍና እና ለልዩ ፍላጎት ትምህርት ተማሪዎች ተጨማሪ ድጋፍ ይሰጣሉ ፡፡ 

 ጃምፕ ስታርት የሚሰጠው መቼ ነው? 

ጃምፕ ስታርት በኣካል ለመስጠት አቅደናል፣ነገር ግን ይህ ከተለወጠ ትምህርት ቤትዎ ያገኝዎታል።ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ያደርሳሉ ከትምህርት ቤት ይወስዳሉ -የትምህርት ቤት የአውቶቡስ መጓጓዣ አይሰጥም።ቁርስ እና ምሳ በነጻ ይሰጣሉ። 

 ለጃምፕ ስታርት እንዴት መመዝገብ አለብን? 

ትምህርት ቤቶች ወደ ትምህርት ቤታቸው የተመደቡ ቤተሰቦችን የጃምፕ ስታርት የምዝገባ መረጃ በፀደይ ይልካሉ።ለማንኛውም ጥያቄ ወደ ትምህርት ቤትዎ ይደውሉ። 

 የሚከተሉትን ካልዎት እባክዎን የጃምፕ ስታርት ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ወደ የልጅዎን ትምህርት ቤት ይደውሉ: 

 • ልጅዎ በትምህርት ቤት ውስጥ መድሃኒት ወይም የጤና እንክብካቤ የሚያስፈልገው ከሆነ(ከሆነች) 
 • ልጅዎ IEP ካለው ወይም ልንሰጠው የምንችል ተጨማሪ ድጋፍ ካለ 
 • ቤተሰብዎ የመጓጓዣ ወይም የልጆች እንክብካቤ እርዳታ የሚፈልጉ ከሆነ