Seattle Public Schools

Resources

Naviance

ናቪያንስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ከዚያ በላይ እቅድ

ናቪያንስ ከሲያትል ት/ቤቶች በኋላ ላለው ህይወት ተማሪዎቻችንና ወላጆቻቸው መዘጋጀት እንዲችሉ ያገለግላል።በናቪያንስ ተማሪዎች የኮሌጅና የስራ አቅጣጫዎቻቸውን ይፈትሻሉ፥ ከስራና ከባህሪያቸው ጋር ተያይዞ ያለውን ክህሎትና ችሎታ ይገመግማሉ፥ እንዲሁም በአካዳሚክ ግባቸው ላይ የሚያደርሳቸው መስመር ላይ ለመቆየት እቅዶችን ያዘጋጃሉ።

ይፈትሹ ልዩ የሚያደርግዎት ምንድነው.

በናቪያንስ ያለው የጥንካሬ መፈተሻ ዲዛይን የልጅዎትን በመውጣት ላይ ያሉ ሶስት ክህሎቶችን በመለየት እና በትምህርት: በስራ እና በህይወት ላይ በመተግበር ዉጤታማ ከማድረግ አኳያ ጥንካሬዎች ላይ ያተኮረ ስትራቴጂን ያካትታል::.

ያያይዙ ፍላጎትዎን ከስራዎች ጋር.

ልጅዎትን ከሚያስደስት እንቅስቃሴዎች: የግል ባህርያት: እና የትምህርት ዓይነቶች ፍላጎት ላይ በመነሳት በናቪያንስ ላይ ያለው የስራ ምድቦችን የሚፈልገው
ሰርቬይ የትኛው የስራ መደብ የልጅዎትን ፍላጎት እንደሚያሟላ በደረጃ ያስቀምጣል::
በናቪያንስ ውስጥ ባለው የስራ ፍላጎት ፕሮፋይለር ተማሪዎት ከስራ ፍላጎቱ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን ይመልሳል እንዲሁም ተዛማጅ በሆኑ የስራ አይነቶች ላይ አስተያየቶችን ያገኛል:: ስራዎች በሚፈልጋቸው ዝርዝሮች ውስጥ ይጨመራሉ::

ይመርምሩ

ለስራ ሊያዘጋጁህ የሚችሉ ኮሌጆችና ዋና ዋና ትምህርቶች ከጥንካሬዎት: ፍላጎትዎትና ከግል ባህሪዎ ጋር አብረው የሚሄዱ ናቸው::

ናቪያንስን በመጠቀም ፕላን ያዘጋጁ.

ረዚዩሜ/የህይወት ታሪክ ማዘጋጀት – ልጅዎት የት/ቤት ስራዎችን: የግል ሽልማቶችን : የበፈቃደኝነት አገልግሎት ልምዶችን ክህሎቶችን: እና ሌሎችንም ይህንን ሞጅዩል መሰረት ያደረገ መሳሪያን በመጠቀም መዝግቦ ማስቀመጥ ይችላል::
የኮሌጅ ማመልከቻ ሂደት – ልጅዎት የሚያስባቸውን ኮሌጆችና የማመልከቻውን ዝርዝር ይያዙ – እንዲሁም ለኮሌጆች የሚላከውን የኤሌክትሮኒክ ትራንስክሪፕት ይጠይቁ::
አካባቢያዊና አገር አቀፍ የስኮላርሽፕ ዳታ ቤዝ – ተማሪዎ ሊያመለክቷቸው የሚችሏቸው በሺዎች የሚቆጠሩ የአካባቢና አገር አቀፍ ስኮላርሽፖች አሉ::
የ2ኛ ደረጃና ከዚያም ያለፈ የትምህርት ዕቅዶች – የት/ቤት ሰራተኞች ከ 8ኛ -12ኛ ክፍል ያለውን የ2ኛ ደረጃና ከዚያም ያለፈ የትምህርት ዕቅድ ለማስተላለፍ ናቪያንስን ይጠቀማሉ:: የ2ኛ ደረጃና ከዚያም ያለፈ የትምህርት ዕቅድ የመመረቂያ መስፈርት ሲሆን ተማሪዎትና አማካሪያቸው የመመረቂያ መስፈርቱ መሟላቱንና ከተለየው ግብ ጋር የሚሄድ መሆኑን እርግጠኛ እንዲሆኑ ይረዳቸዋል::

የመረጃ ደህንነት

የሲያትል የህዝብ ት/ቤቶች ለመረጃ ደህንነትና ጥበቃ ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣል:: የናቪያንስ ፖሊሲና አሰራር የመረጃ ደህንነትንና የተማሪን ፕራይቬሲ አስመልክቶ በሚገባ የኋላ ጥናት ያደርጋል:: በፕራይቬሲ ፖሊሲያቸው መሰረት ናቪያንስ የተማሪ መረጃን አይሸጥም ወይንም ለንግድ አገልግሎት አይጠቀምበትም:: በተጨማሪም ለዚህ መሳሪያ በዚህ ኮንትራት ላይ በተቀመጠው የመረጃ ጥበቃና ፕራይቬሲ መስፈርት መሰረት ናቪያንስ መመራቱን ለማረጋገጥ አጠቃላይ የመረጃ ልውውጥ ስምምነት ተግባራዊ ይደረጋል::

የዳታ ፊልዶች

የሚከተለው መረጃ የመሳሪያውን ውጤታማነት ከፍ ለማድረግና ተማሪዎች የሚፈልጉትን ተገቢ የሆነ ድጋፍ ማግኘታቸውን ለማረጋገጥ በናቪያንስ ላይ ይጫናል : የተማሪው የመጀመሪያና የመጨረሻ ስም: ዩዘር ኔም: የፕሮክሲ አይዲ: ት/ቤት: የክፍል ደረጃ: የትውልድ ቀን: ትራንስክሪፕት: ኮርሶች: ጂፒኤ: የኤሲቲ/ሳት ነጥቦች: ዘር እና ጾታ ናቸው:: አማካሪዎች ቀጥተኛ የሆነ ድጋፍና እርዳታ (ለምሳሌ: የኮሌጅ ባውንድ ስኮላርሽፕ ተቀባዮችን: የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተማሪዎችን: ረኒንግ ስታርት: ልዩ ትምህርት) ማድረግ እንዲችሉ የተማሪዎች ቡድኖች መፍጠር ይቻላል:: ሚስጥራዊነቱ መጠበቁን ከማረጋገጥ አኳያ እነዚህ ቡድኖች ከቡድናቸው ስም ይልቅ በፕሮክሲ በመጠቀም እንዲለዩ ይደረጋል::.

Naviance Opt-Out Window

ተማሪዎቻቸው ናቪያንስን እንዳይጠቀሙ የሚፈልጉ ወላጆች ምርጫቸውን በሶርስ ላይ በማሳየት ናቪያንስን ያለመጠቀን ይችላሉ:: ይህንን ያለለምረጥ ጊዜ ነሐሴ 16 እስከ መስከረም 24 ነው::

ለተጨማሪ መረጃ Naviance ይጎብኙ::