Seattle Public Schools

Family Resources

High School and Beyond Plan – SchooLinks (am)

SchooLinks – የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እና የድህረ-ሁለተኛ ደረጃ እቅድ (High School and Beyond Plan – HSBP)

SchooLinks logo

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እና የድህረ-ሁለተኛ ደረጃ እቅድ(The High School and Beyond Plan (HSBP)፣ የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ከ6ኛ ክፍል ጀምሮ የስራ መስኮችን ወይም የኮሌጅ አማራጮችን እንዲያስሱ ለመርዳት የተዘጋጀ የስቴቱ የምረቃ መስፈርት ነው።ተማሪዎች በሚከተሉት ሦስት መሪ ጥያቄዎች ላይ በማሰላሰል ያተኩራል፡

  • እኔ ማን ነኝ?
  • ምን መሆን እችላለሁ?
  • እንዴት ያንን መሆን እችላለሁ?

ተማሪዎች ዓመቱን ሙሉ የሚለዋወጡ ፍላጎቶቻቸውን እና ግቦቻቸውን ለማንፀባረቅ የHSBP ግቦቻቸውን ያዘምናሉ፣ የተማሩትን እና የሚያዳብሯቸውን ክህሎቶች ከወደፊት የሙያ ጎዳናዎች ጋር ያገናኛሉ።ከ6ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች የሚከተሉትን ለማድረግ SchooLinksን ይጠቀማሉ፡

  • የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እና የድህረ-ሁለተኛ ደረጃ እቅድ (HSBP) እንቅስቃሴዎችን ማጠናቀቅ።
  • ሙያዎችን እና ፍላጎቶችን ማሰስ።
  • የምረቃ እቅዶችን መገንባት እና ማዘመን።
  • ኮሌጆች፣የሙያ ማሰልጠኛዎች (apprenticeships)፣የወታደራዊ አገልግሎትን እና ሌሎች የድህረ-ሁለተኛ ደረጃ የሙያ መስመሮችን መመርመር።
  • ስኮላርሺፕ እና ሌሎች እድሎችን መፈለግ።
  • የኮሌጅ እና የሙያ እቅድ ማውጣት እንቅስቃሴዎችን መከታተል።

የተማሪዎች የSchooLinks መዳረሻ(መግብያ)

ተማሪዎች መስከረም 2 ጀምሮ SchoLinks መጠቀም ይችላሉ።

የመግቢያ መመሪያዎች:

  1. ወደ Clever Student Portal ይግቡ ።
  2. ኮሌጅ እና ስራ ዝግጁነት(College Career Readiness) የሚለውን ክፍል ይፈልጉ ።
  3. በClever ዳሽዎርድዎ ላይ በቀላሉ ለማግኘት SchooLinksን ወደ ተወዳጆችዎ (Favorite) ያክሉት ።
  4. SchooLinks መተግበሪያን ይምረጡ (ይጫኑ) ።

የተማሪ ድጋፍ

ተማሪዎች በሚከተሉት መንገዶች ድጋፍ ያገኛሉ፡

  • ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እና የድህረ-ሁለተኛ ደረጃ እቅዳቸው ጋር የተያያዙ የክፍል ትምህርቶች
  • ከትምህርት ቤት መካሪዎች እና ሰራተኞች የሚሰጥ መመሪያ
  • የደረጃ በደረጃ ማስተማሪያ መሰረታዊ መመሪያዎች እና ግብዓቶች

ቤተሰቦች ተማሪዎችን በቤት ውስጥ ለመደገፍ የሚረዱ መረጃዎችንም ያገኛሉ።


የወላጆች/አሳዳጊዎች የSchooLinks መግብያ

SchooLinks ቤተሰቦች የሚከተሉትን እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል:

  • የተማሪዎን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እና የድህረ-ሁለተኛ ደረጃ እቅድ (HSBP) እንዲሁም እድገት ማየት
  • የኮሌጅ እና የሙያ አማራጮችን በጋራ ማሰስ
  • ስለ ጠቃሚ ምዕራፎች እና ቀጣይ እርምጃዎች መረጃ ማግኘት

የወላጆች/አሳዳጊዎች ግብዓቶች:

የመግቢያ መመሪያዎች:

ቤተሰቦች ከመስከረም 2 ጀምሮ SchooLinks መጠቀም ይችላሉ።

  1. ከታች ካሉት አማራጮች አንዱን በመጠቀም ወደ SchooLinks ይግቡ:
    1. በዲስትሪክቱ ፋይል የጉግል (Google)፣ማይክሮሶፍት (Microsoft) ወይም ሊንክዲን (LinkedIn) ኢሜይል ካለዎት በጉግል፣ማይክሮሶፍትወይምሊንክዲንይግቡ(Login with Google, Microsoft, or LinkedIn) የሚለውንይጫኑ።
    2. የይለፍ ቃል ረስተዋል (Forgot Password) የሚለውን ይጫኑ፣በዲስትሪክቱ ፋይል  ያለውን ኢሜይል ያስገቡ፣ከዚያም የይለፍ ቃል(password) ለመፍጠር በኢሜል የተላኩልዎትን መመሪያዎች ይከተሉ።
SchooLinks login page. Click Login with Google, Microsoft, or LinkedIn if you have a Google, Microsoft, or LinkedIn email on file with the district. Or click forgot password.
Click to enlarge
  1. አንዴ ከገቡ በኋላ፣ተማሪዎችዎን ለማየት በላይኛው ክፍል ላይ የሚገኘውን የእኔ ተማሪዎች (My students) የሚለውን ይጫኑ።
    1. ትክክለኛዎቹን ተማሪዎች ካላዩ፣እባክዎን ማስተካከያ ለማግኘት ዲስትሪክቱን ያነጋግሩ።
  2. የተማሪዎን መዝገብ (casefile) ለማየት የተማሪዎን ስም ይጫኑ።ከመዝገቡ ውስጥ የተማሪዎን የግምገማ ውጤቶች ማየት፣የኮርስ እቅዶችን መገምገም፣አማካሪያቸውን ማነጋገር እና ሌሎችንም ማድረግ ይችላሉ!

ጥያቄዎች?

ጥያቄዎች ካሉዎት፣እባክዎን የትምህርት ቤቱን አማካሪ ቡድን ያነጋግሩ(contact the School Counseling team