Skip To ContentSkip To Content

  ለላቀ/ከፍ ላለ ትምህርት/አድቫንስድ ለርኒንግ/ መጠቆሚያ ቅጽ

  ለላቀ/ከፍ ላለ ትምህርት(አድቫንስድ ለርኒንግ)የመጠቆምያ ጊዜ ከነሐሴ 28-ታሕሳስ 7፣2020

  አስፈላጊ : ለ 2021-22 የትምህርት ዓመት ለላቀ ትምህርት ብቁ መሆንን ለመወሰን በ 2020-2021 መከር/ክረምት ወቅት የሚሰጥ ፈተና

  በሲያትል የህዝብ ት /ቤቶች ውስጥ ያሉ ሁሉም ትምህርት ቤቶች የእያንዳንድ ተማሪ አካዴሚያዊ ፣ ማህበራዊ ፣ ስሜታዊ እና ስነምግባራዊ ፍላጎቶች ለማሟላት የተነደፈ ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት ዝግጁ ናቸው ፡፡

  የላቀ ትምህርት ዲፓርትመንት የእያንዳንዱን ልጅ ልዩ ችሎታዎች እና ተሰጥኦዎች ለማዳበር ቁርጠኛ ነው። ልጅዎ ተመሳሳይ ዕድሜ ካላቸው የክፍል ጓደኞቻቸው ባሻገር ልዩ ክህለቶች፣ወይም የመማር እና የማመዛዘን ችሎታ እያሳየ ከሆነ፣  ልጅዎን ለከፍተኛ ችሎታ ያላቸው ( Highly Capable) ወይም ለላቀ ( Advanced Learning) ትምህርት አገልግለቶች ግምገማ  መጠቆም ይችላሉ።

   

  ወደ ላቀ ትምህርት ለመግባት ላሳዩት ፍላጎት እናመሰግናለን።በ ኮቪድ-19 ምክንያት አፈፃፀማችን ተቀይሯል።የላቅ ትምህርት መጠቆምያ(ማመልከቻ)ጊዜ በጊዜው ነሓሴ 28 ይከፈታል፣ ነገር ግን ሲያመለክቱ የፈተና ቀንን እንዲመርጡ አይጠየቁም። ትምህርት ቤቶች መቼ እና እንዴት መልሰው እንደሚከፈቱ መገመት ስለማንችል ፣በዚህ ጊዜ የፈተና ቀኖችን መወሰን አልቻልንም።

  ለላቀ ትምህርት ካመለከቱ፣ወደ ትምህርት ቤቶች መመለስ ከተፈቀደ በኋላ የፈተናውን የጊዜ ሰሌዳ መረጃ በ ኢሜል ይላክልዎታል። በሁለት ወይም ከዚያ በላይ ጣቢያዎች ቅዳሜ ላይ መፈተን ፣ ወይም የቅይጥ(ከፊል በአካል፣ከፊል በርቀት)የትምህርት ሞዴልን ከተፈቀደ በትምህርት ቤት ውስጥ መፈተን የሚሉትን ጨምሮ በርካታ ሞዴሎችን እየተመለከትን ነው። ቢያንስ እስከ ጥር 2021 ድረስ የሆነ አማራጭ አይጀምርም ፡፡

  በሲያትል የህዝብ ት / ቤቶች ውስጥ ያሉ ሁሉም ትምህርት ቤቶች የእያንዳንዱን ተማሪ አካዴሚያዊ ፣ ማህበራዊ ፣ ስሜታዊ እና ስነምግባራዊ ፍላጎቶች ለማሟላት የተነደፈ ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት ዝግጁ ናቸው ፡፡

   

  ልጄ ለከፍተኛ ትምህርት ወይም ለልዩ ተሰጥኦ ያላቸው አገልግሎቶች ምዘና መጠቆም(መጠየቅ)አለብኝ?

  የከፍተኛ ትምህርት ዲፓርትመርንት የእያንዳንዱን ልጅ ልዩ ችሎታ እና ተሰጥዖ ለማዳበር ቁርጠኛ ነው። ልጅዎ ከዕድሜ እኩዮቹ በላይ የመማር እና የማመዛዘን ልዩ ችሎታ ወይም ተሰጥዖ እያሳየ ከሆነ፣ልጅዎ የከፍተኛ ትምህርት ወይም የልዩ ተሰጥዖ ያላቸው ተማሪዎች አገልግለቶች ለማግኘት ለግምገማ እንዲያመለክቱ የመከራሉ።

  ለምሳሌ ፣ ልጅዎ በሚከተሉት ዘርፎች ልዩ ችሎታዎችን ማሳየት ይችላል:

  የአመራር ፣ የፈጠራ ፣ የተነሳሽነት እና የመማር

  ከዕድሜ እኩዮቹ በላይ የሚያሳያቸው(የምታሳያቸው)ችሎታዎች:

  • አመራር(Leadership)
   • በራስ የሚተማመን እና ሁኔታዎችን ማደራጀት እና መዋቅር የሚችል ጠንካራ ተግባቢ ሊሆን ነው።
  • ፈጠራ(Creativity)
   • በከፍተኛ ሃሳባዊ( ምናባዊ)እና የፈጠራ ሀሳቦች እና/ ወይም መፍትሄዎችን የማምጣት ችሎታ ሊያሳይ ይችላል።
  • ተነሳሽነት(Motivation)
   • በመጀመሪያ አስደሳች እና /ወይም በርዕሱ ላይ ፍላጎት ሲኖረው ፣የረጅም ጊዜ ፕሮጀክት ለመስራት ከተስማም፣ በዚህ ስራ ለመቀጠል ውጫዊ ተነሳሽነት ብዙም የማይፈልግ ሊሆን ይችላል።
  • የመማር (Learning)
   • ስለ አንድ የተወሰነ ርዕሰ ጉዳይ ሰፋ ያለ የመረጃ ክምችት ሊኖሮው ይችላል እና /ወይም ብዙውን ጊዜ ጠንቃቃ ወይም አስተዋይ ምልከታዎችን ሊያደርግ ይችላል።

  ትምህርታዊ(Academic)

  ከዕድሜ እኩዮቹ በላይ የሚያሳያቸው(የምታሳያቸው)ችሎታዎች:

  • ሒሳብ
  • ንባብ
  • ፅሁፍ
  • ሳይንስ

  ያልተገለፀ

  እንዲሁም ተማሪዎ እዚህ ያልተዘረዘሩ እና በቀላሉ የማይገለፁ ልዩ ችሎታዎችን እያሳየ ሊሆን ይችላል።

  የልጅዎ ችሎታዎች በክፍል ውስጥም ሆነ ከክፍል ውጭ ሊታዩ ይችላሉ። . ከላይ የተዘረዘሩት ሁሉም ችሎታዎች በተለያዩ ቦታዎች እና ተግባራት ውስጥ ሊታዩ ይችላሉ ፣ ለምሳሌ::

  • በዕለት ተዕለት ተግባሮች
  • በግምገማዎች
  • በአንድ ፕሮጀክት ውስጥ ሲሳተፉ
  • በትርፍ ጊዜ ሲሰሩ
  • ቤት ውስጥ
  • ከት / ቤት እንቅስቃሴዎች በፊት / በኋላ
  • በማህበረሰብ ማዕከል

  ብዙ ቋንቋዎችን ለሚናገሩ ተማሪዎች፣እነዚህ ችሎታዎች በማንኛውም ቋንቋ ሊታዩ ይችላሉ ፡፡.

  ከተለያዩ ሞያዎች የተውጣጡ የምርጫ ኮሚቴ ወይም MSC (WAC 392-170-070)ለ ልዩ ተሰጥዖ ያላቸው ወይም ለከፍተኛ ትምህርት አገልግሎቶች ብቁነትን ለመወሰን ያሉትን ሁሉንም ማስረጃዎች ይመረምራል። የላቀ ትምህርት ዲፓርትመንት የኮቪድ -19 ምርመራ በሚመለከት የስቴት ሕግ እና የአከባቢ መስፈርቶች የሚያሟላ የመለያ ዕቅድ ለማዘጋጀት ከስቴት ባለሥልጣናት እና ከሃገራዊ ተመራማሪዎች ጋር እየሠራ ነው ፡፡ቤተሰቦች በሕዳር ወር ዝመናዎችን ይደርሳቿል።

  እባክዎን፣ተማሪዎች በአንዳንድ መስኮች ልዩ ችሎታዎችን ሲያሳዩ በሌሎች መስኮች ደግሞ ድክመቶችን ማሳየት የተለመደ መሆኑን ልብ ይበሉ። ልጅዎ ልዩ ችሎታዎችን እያሳየ ከሆነ፣ የልጅዎን ልዩ ችሎታዎች እና ተሰጥዖዎች እድገት መደገፍ እንድንችል፣እባክዎን ለልጅዎ ለላቀ ትምህርት ወይም ለከፍተኛ ተሰጥዖ ያላቸው አገልግለቶች ግምገማ ያመልክቱ።

   

  የወላጅ/ኣሳዳጊ ፍቃድ መስጫ ቅድ (የግድ መሞላት ኣለበት)

  ለላቀ/ከፍ ላለ ትምህርት(አድቫንስድ ለርኒንግ)የመጠቆምያ ጊዜ ከነሐሴ 28-ታሕሳስ 7፣2020

  Parent Referral Form

   

  ማናቸውም ጥያቄዎች ካሉዎት እባክዎን ጽ / ቤታችንን በሚከተለው ያነጋግሩ: advlearn@seattleschools.org  ወይም 206-252-0130

  To refer in English, please go to The Source