Skip To ContentSkip To Content

  ለልጆቻችን የ Seattle ደህንነት እንጠብቅ፡፡ ህጉን ይወቁ! 

   

   

  የ Seattle የህዝብ ት/ቤቶች ለተማሪዎች ደህንነት ከፍተኛ ቅድሚያ ይሰጣሉ፤ የት/ቤት ባስ የደህንነት ካሜራ መርሀግብር በማህበረሰባችን ውስጥ ለሚገኙ ተማሪዎች ከት/ቤት ባስ የመውጣት እና ወደ ባሱ የመግባት ደህንነትን ያግዛል፡፡ 

   

  ስርአቱ እንዴት እንደሚሰራ 

  1. መለየት
  2. አጭር መግለጫ
  3. የሰሌዳ ቁጥር

   

   

  የቪድዮ ካሜራዎች በባሱ የውጪ ክፍል ቁልፍ በሆኑ ቦታዎች ላይ ይገጣማሉ፡፡ 

  ባስ 'ቁም' የሚለውን ክንፉን ሲዘረጋ ተግባራዊ በሚደረግበት ዞን ውስጥ መኪና የቆመውን የት/ቤት ባስ አልፎ መሄዱን ስርአቱ ወዲያው ይለያል፡፡ 

  መኪና የት/ቤት ባስን አልፎ ከሄደ ካሜራው ጥፋተኛውን ተሽከርካሪ የሚያሳየውን ቪድዮ ይቀርጻል፡፡ 

  ከቪድዮው የተቀነጨበው ጥፋት የሚያሳየው ምስል የሚያሳየው ጥፋተኛው ተሽከርካሪ የት/ቤቱን ባስ አልፎ ሲሄድ ብቻ ሳይሆን የተሸከርካሪውን የሰሌዳ ቁጥር እና የባሱ የተዘረጋውን ቁም የሚለውን ክንፉንም ጨምሮ ነው፡፡ የጥፋተኛው ተሽከርካሪ ቪድዮ ለተፈጸመው ጥፋት እንደማስረጃነት ይቀመጣል፡፡ 

  ጥፋት የሚያሳየው ምስል እና ቪድዮ የመጨረሻ ግምገማ በህግ አስከባሪ ሰዎች ይደረጋል፤ ከዛም ጥፋተኝነቱን ያጸድቃሉ ወይም ይሽራሉ፡፡ 

  ጥፋተኝነቱ ከጸደቀ  

   

   

   

  ለት/ቤት ባስ መቼ እንደሚቆም 

  RCW 46.61.370: የት/ቤት ባስ የ 'ቁም' ምልክቱን ሲያሳይ እና ቀይ መብራችን ሲያበራ ሞተረኞች መቆም አለባቸው፡  

  ባለሁለት መስመር፣ ያልተከፈለ መንገድ፡፡ 

   

  የት/ቤት ባስ ለተሳፋሪዎች ሲቆም ከሁለቱም አቅጣጫ የሚመጡ ሁሉም ትራፊክ መቆም አለባቸው፡፡

   

  ባለሶስት ወይም ከዛ በላይ መስመር ያለው ያልተከፈለ መንገድ፡፡

   

  የት/ቤት ባስ ለተሳፋሪዎች ሲቆም መጓዝ የሚችሉት በተመሳሳይ አቅጣጫ የሚጓዙ ተሸከርካሪዎች ብቻ ናቸው፡፡

   

  ወደሁለት የተለያየ መጓዣ አቅጣጫ የተከፈለ መንገድ፡፡

   

  የት/ቤት ባስ ለተሳፋሪዎች ሲቆም መጓዝ የሚችሉት በተመሳሳይ አቅጣጫ የሚጓዙ ተሸከርካሪዎች ብቻ ናቸው፡፡

   

  በተከፈለ እና ባለብዙ መስመር መንገድ የሚመጣ ትራፊክ መቆም የለበትም፡፡ ተማሪዎች የእንደዚህ አይነት መንገዶችን እንዲሻገሩ የሚያስገድድበት መንገድ ላይ የት/ቤት ባሶች ማቆም አይችሉም፡፡

   

  ቶሎ ቶሎ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

   

  የት/ቤት ባስ የደህንነት ካሜራዎቹ የተገጠሙት የት ነው? 

  የት/ቤት ባስ የደህንነት ካሜራዎች የተገጠሙት በ የህዝብ ት/ቤቶች ባሶች የውጪ ክፍል ቁልፍ ቦታዎች ላይ ተገጥመዋል፡፡ 

  የመጨረሻው መጠን ምን ያህል ነው እና የመንዳት መሀደሬስ?  

  የመጨረሻው መጠን $419 ነው፡፡ ይህ የፍትሐብሄር ቅጣት ነው፤ ነጥቦች አይያዙም፡፡ 

  ለት/ቤት ባስ የማቆመው መቼ እና የት ነው? 

  የት/ቤት ተሽከርካሪ የሚቆመው ተቀያያሪው ቀይ መብራት ሲበራ፣ የ'ቁም' ምልክቱ ወጥቶ ሲበራ ነው፡፡   ማቆም ያለብዎት ከት/ቤት ተሽከርካሪው ቢያንስ 20 እግር ከፊት እና 20 እግር ከኋላ ርቀው ነው፡፡ 

  የሚበራ መብራት ስርአት 

  ቀይ እና አምበር መብራቶች አሉ፡ በት/ቤቱ ተሽከርካሪ አናት ላይ የሚገኝ፡፡  አላማው የት/ቤቱ ተሽከርካሪ ለማቆም እየተዘጋጀ እንደሆነ ለሌሎች ሞተረኞች ለማስጠንቀቅ ነው፡፡ 

  ማቆም አለብዎት - ህግ ነው፡፡