Information and Resources
የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ዜና
የተማሪ ምግቦች
የሲያትል የህዝብ ት/ቤቶች ተማሪዎች ከምግብ ማሰራጫ ትምርህርት ቤቶች እና ከአውቶቡስ ፌርማታዎች ሊወስዱት የሚችሉ ምግብ አላቸው። የማኅበረሰብ ፍላጎትን ለማሟላት የምግብ ማሰራጫ ትምህርት ቤቶች እያሰፋን ነው እና አንዳንድ የአውቶቡስ ፌርማታዎች ይቀየራሉ። የምግብ ማሰራጫ ትምህርት ቤቶች፣የአውቶቡስ መስመር ካርታዎች እና የጊዜ ሰሌዳዎች በየተማሪ ምግብ ድረ ገጻችን ( student meal webpage)ላይ ማግኘት ይችላሉ ፡፡ የምግብ ማሰራጫ ጣብያዎች ከመስከረም 4 ጀምሮ፣ ከሰኞ- ከዓርብ፣ከ 11:15 a.m.–1:15 p.m ክፍት ይሆናሉ።
ከአንድ በላይ ተማሪ ያላቸው ቤተሰቦች በአንድ ጊዜ ብዙ ምግቦችን መውሰድ ይችላሉ፡፡በተጨማሪም በየቀኑ ወደ ጣብያው ወይ ወደ የኣውቶቡስ ፌርማታ ከመሄድ ምግባቸውን በአንዴ ለመውሰድ የሚፈልጉ ተማሪዎች ከአንድ በላይ ምግብ ሊወስዱ ይችላሉ።
Technology
Devices
አዲሱን ላፕቶፕዎን ይተዋወቁ!
ስለ የትምህርት መሳርያዎ ቪዲዮዎች
በ Schoology፣Seesaw፣ወይም Teams ላይ እገዛ ይፈልጋሉ? የተተረጎሙ ስሪቶችን ጨምሮ አዲስ how-to videos አሁን በ SPSTV YouTube channel ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ቪዲዮዎች እንዴት እንደሚገቡ፣የተማሪዎን የትምህርት ኮርሶች እንዴት እንደሚዳስሱ ፣አሳይሜንቶች እንዴት እንደሚያስረክቡ፣እና ሌሎች ያስተምራሉ።