Language Testing
ከእንግሊዘኛ ውጪ ሌላ ቋንቋ ያውቃሉ? በቋንቋውም ማንበብ እና መፃፍ ይችላሉ?
የዓለም ቋንቋ ክሬዲት ፈተና የ2021-2022መረጃ
ለሲያትል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተማሪዎች:
- ብቁ ስለመሆንዎ ወይም አለመሆንዎ እና የትኞቹን ፈተናዎች መውሰድ እንደሚችሉ እዚህ ይመልከቱ
- ስለ የፈተና ቀናት የሁለተኛ ደረጃ ት/ ቤትዎ አማካሪ ያነጋግሩ ወይም ለየዓለም ቋንቋ ክሬዲት ፈተና በመስመር ላይ ይመዝገቡ። ፈተናው በ Microsoft Teams በርቀት ይሆናል። የተወሰኑ የበአካል ፈተና አማራጮች በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ ሊገኙ ይችላሉ።
በሲያትል የህዝብ ት/ቤቶች ለሚማሩ የ 8ኛ፣የ9ኛ፣የ10ኛ፣ የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የፈተና ወጪያቸውን ስፖንሰር ተደርገዋል።
በቋንቋዎ ከ 1-4 የዓለም ቋንቋ ክሬዲት ለማግኘት፣ቀጥሎ ያሉትን የመስራት ችሎታዎ ምን ያህል ነው?
- በሐረጎች፣በአጫጭር ዓረፍተነገሮች እና በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ በሚውሉ አገላለጾች የሚገለፁ የተለመዱ ርዕሶች ሀሳባቸውን መረዳት እችላለሁ፡፡
- የተለመዱ ቃላት የያዙ የቀላል ጽሑፎች ዋና ሀሳብ እና አንዳንድ ዝርዝሮች መረዳት እችላለሁ።
- ስለ የተለመዱ ተግባሮች፣ርዕሶች እና እንቅስቃሴዎችን አስመልክቶ ከሌላ ሰው ጋር መረጃዎችን መለዋወጥ እችላለሁ።
- በተለመደ ርዕስ ዙሪያ ላይ መሰረታዊ መረጃዎችን ለማቅረብ ተከታታይ ሃረጎችንና ዓረፍተ ነገሮችን መጠቀም እችላለሁ።
- ቀላል መግለጫዎችን እና አጫጭር መልዕክቶችን መጻፍና በተለመዱ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጥያቄዎችን መጠየቅና መረጃዎችን ማቅረብ እችላለሁ።
መጪዎቹ የፈተና ቀናት: ሁሉም የፈተና ቀኖች ቅዳሜዎች ናቸው
- ጥቅምት 2፣2021
- ጥቅምት 30፣2021
- ህዳር 20፣2021
- ታህሳስ 11፣2021
- ጥር 29 ፣ 2022
- የካቲት 26፣2022
- መጋቢት 26፣2022
- ሚያዚያ 30፣2022
ቦታ: የዚህ ዓመት ፈተና በMicrosoft Teams በመጠቀም በርቀት በመስመር ላይ ይሰጣል።የበአካል ፈተና ቀናት በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ ሊለቀቁ ይችላሉ።
ማሳሰብያ: የት/ቤትዎን አማካሪ ያነጋግሩ።የ2ኛ ደረጃ ት/ቤትዎ ምናልባትም ፈተናውን በሌላ ቀናት ሊሰጥ ይችል ይሆናል።
ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተለውን አገናኝ ይመልክቱ:
Qጥያቄዎች? እባክዎ Gosia Stoneን በ 206-252-0691 ወይም በ mjstone@seattleschools.org ያነጋግሩ።