Back-to-School Health Guidance 

Summary: Together we can keep our schools healthy and thriving throughout the upcoming school year and beyond. 

ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ የጤና መመሪያ 

በሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች ጤና እና ደህንነት ናቸው።በ2022-23 የትምህርት ዘመን የትምህርት ቤታችን ማህበረሰቦች ጤንነት ለመጠበቅ ከሰራተኞች እና ቤተሰቦች፣እና ከየአካባቢያችን እና የስቴት የህዝብ ጤና ኤጀንሲዎች -ከዋሽንግተን ስቴት የጤና ዲፓርትመንት እና–የሲያትል እና ኪንግ ካውንቲ የህዝብ ጤና ጋር አጋር መሆናችንን እንቀጥላለን።  

የተማሪዎችን እና የሰራተኞችን ጤንነት መጠበቅ 

ለ2022-23 የትምህርት ዘመን ጤናማ ወደ ትምህርት ቤት መመለስ ለማረጋገጥ ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች እየወሰዳቸው ያሉ አንዳንድ እርምጃዎች የሚከተሉት ናቸው። 

ክትባቶች እና ቡስተሮች – የኮቪድ-19 ክትባቶች እና ቡስተሮች በኮቪድ-19 ከሚመጣ ከባድ በሽታ የሚጠብቁ የተሻሉ መከላከያ ናቸው።ቤተሰቦቻችን፣ትምህርት ቤቶቻችን እና አጋር የህክምና አቅራቢዎቻችች ላደረጉት ጥረት ምስጋና ይድረሳቸው እና ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች በአገሩ ውስጥ ካሉ ከፍተኛ የክትባት መጠን ካሏቸው የትምህርት ዲስትሪክት አንዱ ነው።ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች የክትባት እና የቡስተር ክሊኒኮች ማቅረቡን ይቀጥላል።ወቅታዊ ቀኖችን እና ቦታዎችን በየሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች የክትባት ድረ ገጽ(SPS Vaccine Page)ይመልከቱ።  

ምርመራ – ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች የኮቪድ-19 ምርመራ(COVID-19 testing) በት/ቤቶች መስጠቱን ይቀጥላል።የዋሽንግተን ስቴት ነዋሪዎች በየወሩ እስከ 10 የሚደርሱ ነጻ ምርመራዎችን ከዋሽንግተን ስቴት የጤና ክፍል ማዘዝ ይችላሉ።አብዛኛው ኢንሹራንስ ለአንድ ግለሰብ በወር እስከ ስምንት የሚደርሱ የራስ መመርመርያ ወጪዎች ይሸፍናል። 

የትምህርት ቤት ሕንፃዎች – የሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ህንጻዎች በ የጤና ዲፓርትመንት እና በየአሜሪካ የአየር ማሞቂያ፣ማቀዝቀዣ እና የአየር ሁኔታ መሐንዲሶች ምክሮች የተቀመጡትን የቤት ውስጥ የአየር ጥራት ደረጃዎችን ያሟላሉ።የጋራ ቦታዎች በመደበኛነት ማጽዳት ይቀጥላል። 

ኮቪድ-19 

የጤና ዲፓርትመንት በቅርቡ የትምህርት መጀመሪያ የኮቪድ-19 መመሪያ(COVID-19 guidance) አዘምኗል።እርስዎ እና ተማሪዎ (ችዎ) ወደ አዲሱ የትምህርት አመት ሲገቡ እነዚህን መመሪያዎች ያስታውሱ።ይህ መመሪያ በትምህርት ዓመቱ  ሊለወጥ ይችላል። 

ምልክቶች፣ምርመራ እና ማግለል 

 • ማንኛውም ሰው የኮቪድ-19 ምልክት ሲኖረው(showing symptoms of COVID-19) ቤት መቆየት እና የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግ አለበት።  
 • በኮቪድ-19 መያዙን በምርመራ የተረጋገጠ ሰው ለአምስት ቀናት በቤት መገለል አለበት።ከአምስት ቀናት በኋላ ምልክቶቹ ከተሻሻሉ እና ግለሰቡ ቢያንስ ለ24 ሰዓታት ትኩሳት ከሌለው (ትኩሳት የሚቀንሱ መድሃኒቶችን ሳይወስድ) ወደ ትምህርት ቤት ወይም ወደ ሥራ ሊመለስ ይችላል። ከመመለሳቸው በፊት የኮቪድ-19 ምርመራ ይበረታታል። 
 • አንድ ግለሰብ ከአምስት ቀናት መገለል በኋላ የኮቪድ ምርመራ ውጤቱ አዎንታዊ ከሆነ፣ለ10 ሙሉ ቀናት በቤት መገለል አለበት። 
 • ከተገለለ በኋላ ወደ ትምህርት ቤት ወይም ወደ ሥራ የሚመለስ ማንኛውም ሰው ከስድስተኛው እስከ 10ኛው ቀን ድረስ በደንብ የተገጠመ ማስክ ማድረግ ይኖርበታል።እነዚህ ግለሰቦች በስፖርትም ሆነ በሌሎች ከመደበኛ ትምህርት ውጭ እንቅስቃሴዎች ማስክ ማድረግ አለባቸው። 
 • አንድ ግለሰብ ማስክ በትክክል መልበስ  የማይችል ከሆነ፣ለ10 ቀናት ሙሉ መገለሉን መቀጠል አለበት። 

ቤተሰቦችን ማሳወቅ 

 • ትምህርት ቤቶች ስለ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ቤተሰቦችን እና ሰራተኞችን የማሳወቅ ሂደት እንዲኖራቸው ያስፈልጋል። 
 • ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ተጋላጭ የሆኑ ተማሪዎችን በቀጥታ የማሳወቅ ግዴታ የለባቸውም። 
 • ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች፣በትምህርት ቤቶች ህንፃዎች ውስጥ ያሉትን አጠቃላይ የኮቪድ-19 ጉዳዮች(cases ) በዳሽቦርድ ይይዛሉ።እንዲሁም በትምህርት ቤት ህንፃዎች ውስጥ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተነኩ ቤተሰቦች ጋር በቀጥታ እንገናኛለን።  

በ DOH መሠረት፣ከአሁን በኋላ የሚከተሉትን ነገሮች በሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች መገልገያዎች አያስፈልጉም:  

 • አካላዊ መራራቅ 
 • የመስክ ጉዞ ገደቦች 
 • በትላልቅ ስብሰባዎች እና በሌሎች ስብሰባዎች ላይ የሚደረጉ ገደቦች   
 • ሁለንተናዊ ማስክ (በሕክምና ቦታዎች ካልሆነ በስተቀር) 

ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች፣ሰዎች በትምህርት ቤቶች በሚሆኑበት ግዜ ማስክን መጠቀም በእጅጉ ይመክራል።ትክክለኛ ማስክ በትክክል መጠቀም የኮቪድ-19 ስርጭት ስጋት ይቀንሳል።ተማሪዎች እና ሰራተኞች በትምህርት ቤት እና በህፃናት እንክብካቤ መስጫ ቦታዎች ማስክ ለመልበስ ሊመርጡ ይችላሉ፣የሌሎችን ምርጫ እንደተጠበቀ ሆኖ።ማስኮች በሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ህንጻዎች ውስጥ መገኘታቸውን ይቀጥላሉ። 

ለተጨማሪ መረጃ የሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች የኮቪድ-19 ዳሽቦርድ( SPS COVID-19 Dashboard )እና የኮቪድ-19 ምላሽ ድረ ገጽ( COVID-19 response page)ይጎብኙ።  

የMonkeypox ቫይረስ (MPV) 

በዋሽንግተን ስቴት እና በዩኤስ የሚገኘው ሌላ ተላላፊ በሽታ MPV ነው።ሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ሁሉም ሰራተኞች እና ቤተሰቦች ከዚህ በሽታ ለመዳን የDOH እና PHSKC መመሪያዎችን እንዲያጤኑ ያበረታታል። 

MPV ምንድን ነው? 

MPV ሽፍታ ሊያመጣ የሚችል ኢንፌክሽን ነው – በቆዳ ላይ እንደ እብጠት ወይም ብጉር ሊመስል ይችላል። እንዲሁም የጉንፋን ምልክቶችን ሊያስከትል ይችላል።ቫይረሱ አልፎ አልፎ ለሞት የሚዳርግ ነው ነገር ግን በሽታን የመከላከል አቅማቸው ደካማ ለሆኑ እና ለልጆች፣እና ለእርጉዞች ከባድ ሊሆን ይችላል።  

ቫይረሱ እንዴት ይተላለፋል?  

በ PHSKC መሠረት( According to PHSKC,)፣MPV በሰዎች መካከል በሚኖር የቅርብ፣የቆዳ ለ ቆዳ ንክኪ ሊሰራጭ ይችላል።ማንኛውም ሰው በቫይረሱ ሊያዝ ይችላል።  

በሽታውን እንዴት መከላከል ይቻላል። 

የስቴቱ የጤና ዲፓርትመንት(state DOH recommends) ክፍት ቁስሎች፣ቁስሎች ወይም ሽፍታዎች ካሉት ወይም በMPV ከተያዘ ከማንኛውም ሰው ጋር የቅርብ ወይም የቆዳ-ለቆዳ ንክኪ እንዳይኖር ይመክራል። የቅርብ ግንኙነት ማለት ለብዙ ሰዓታት አብሮ መቆየት፣መተቃቀፍ፣መሳሳም፣አልጋ ወይም ልብስ መጋራትን ሊያካትት ይችላል። 

MPV ከተጋለጡ በተቻለ ፍጥነት ክትባት መውሰድ አስፈላጊ ነው።ይህ ኢንፌክሽንን ሊከላከል ይችላል።ለበለጠ መረጃ  የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ ወይም የአካባቢ ጤና ዲፓርትመንት( local health department)ያነጋግሩ።  

ሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎችን እና ሰራተኞችን ደህንነት ለመጠበቅ ምን እያደረገ ነው። 

ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች፣የትምህርት ቤቶቻችንን ማህበረሰቦች ከMPV ለመጠበቅ፣ከDOH እና PHSKC ጋር በመተባበር እና የእነርሱን መመሪያ በመከተል ላይ ነው። 

የተላላፊ በሽታዎች ስርጭትን ኣስመልክቶ ዲስትሪክቱ እየወሰደው ስላለው ጥንቃቄ ተጨማሪ መረጃ በየሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ድህረ ገጽ(SPS website) እና በየሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች የጤና አገልግሎት ድረ-ገጽ(SPS Health Services webpage

 ላይ ይገኛል።  

ለበለጠ መረጃ እባክዎን የDOH  እና PHSKC ድረ-ገጾችን ይጎብኙ።  

  

You may also be interested in

An illustration of four students, two wear masks two do not

የኳራንቲን እና የግንኙነት ፍለጋ ዝመናዎች

ሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች የኮቪድ-19 መጠንንን በትምህርት ቤቶቻችን መከታተል ይቀጥላል እና አስፈላጊ ከሆነም ለማሻሻል ዝግጁ ነው።…